በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ የዳኝነት አገልግሎት ይሰጣል የተባለ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ተደራጀ

በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ የዳኝነት አገልግሎት ይሰጣል የተባለ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ተደራጀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ  አለመግባባቶች ቢነሱ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ የዳኝነት አገልግሎት ይሰጣል የተባለ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ተደራጀ።

ችሎቱ የተደራጀው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድቤት ሲሆን 10ኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት በሚል ስያሜ በአንድ ችሎት 3 ዳኞች የሚያስችል ነው ተብሏል።

በአጠቃላይ 33 ዳኞች እና 10 ችሎት ተዘጋጅቷል።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ብርሀነመስቀል ዋጋሪ ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት የተደራጀው ችሎት በተለይም በምርጫ ቦርዱ ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት የሚቀርቡ አቤቱታዎች ከመጡ በህግ አግባብ ብቻ በመዳኘት ፈጣን እልባት የሚሰጥ ነው።

የኢትዮጵያ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ  አዋጅ ቁጥር 1133/2011  እንዲሁም ወደፊት የሚወጡ ደንብና መመሪያዎች መሰረት ሀገራዊ ምርጫውን  ለማሳካት ሲባል ቅድሚያ በመስጠት ችሎቱ በፈጣን ሁኔታ እንዲደራጅ መደረጉን ገልጸዋል።

ለችሎቱ አጋዥ የሆኑ የችሎት አስፈጻሚዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ዝግጁ መሆናቸውንም አክለዋል።

በታሪክ አዱኛ

 

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ የዳኝነት አገልግሎት ይሰጣል የተባለ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ተደራጀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply