በ6 ወራት 20 ሚሊዮን ብር አበድሪያለሁ—ኢቲ ኬር የብድር እና ቁጠባ ተቋም

ከተመሰረተ አንድ አመት ያስቆጠረው ኢቲ ኬር የብድር እና ቁጠባ ተቋም በስድስት ወራት ውስጥ 20 ሚሊዮን ብር አበድርያለሁ አለ።

ኢቲ ኬር የብድር እና ቁጠባ ተቋም አንደኛ አመት የምስረታ በአሉን ሲያከብር የኮር ባንኪንግ ሲስተም መጠቀም መጀመሩን አስታወቋል።

ከዚህ በፊት በብድር እና ቁጠባ ተቋማት የማይታሰበው የኮር ባንኪንግ ሲስተም በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ መጠቀም መጀመሩን ነው ያስታወቀው።

ከተመሠረተ አንድ የሆነው የብድር እና ቁጠባ ተቋሙ የተመሰረተበትን አንደኛ አመት የምስረታ በአሉን እያከበረ ይገኛል።

ተቋሙ በአንድ አመት ጉዞው የአባላቱን ቁጥር #ከ600 በላይ ማድረሱን ገልጿል።

እስከ ዛሬ ድረስ #18 የተለያዩ አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝ ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም ተቋሙ በቀጣይ ዲጂታል ዕቁብ ለመጀመር ዝግጅት አድርጎ መጨረሱን አስታውቋል።

የብድርና ቁጠባ ተቋም የሆነው ኢቲኬ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆነውም #14 መኪኖች በመግዛት ለደንበኞቹ እንደሰጠ ታውቋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply