በ7 ወራት ውስጥ ከ700 በላይ ጥቆማዎች እንደቀረቡለት የጸረ ሙስና ኮሚሽኑ አስታወቀ ሙስናና ብልሹ አሰራርን በተመለከተ ባለፉት በ7 ወራት ጊዜ ውስጥ 743 ጥቆማዎችን መቀበሉን የፌደራል የ…

በ7 ወራት ውስጥ ከ700 በላይ ጥቆማዎች እንደቀረቡለት የጸረ ሙስና ኮሚሽኑ አስታወቀ

ሙስናና ብልሹ አሰራርን በተመለከተ ባለፉት በ7 ወራት ጊዜ ውስጥ 743 ጥቆማዎችን መቀበሉን የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ከቀረቡት ጥቆማዎች ውስጥ በቁጥር 632 ወይም 85 በመቶ የሚሆኑት የሙስና ወንጀል ጥቆማዎች ሲሆኑ በቁጥር 111ወይም 15 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የሙስና ወንጀል ያልሆኑ ጥቆማዎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ከቀረቡት የሙስና ወንጀል ጥቆማዎች ውስጥ 2 በመቶ የሚሆኑት ግን አስቸኳይ የሙስና መከላከል ውስጥ የተካተቱ ናቸው ተብሏል፡፡

የቀረቡት የሙስና ወንጀል ጥቆማዎች በህገወጥ የመሬት ወረራ፣ ከህግና መመሪያ ውጭ የተካሄዱ የመንግስት ግዥና ጨረታ፣ በሰው ሀይል ቅጥር ፣ዝውውር ፣ምደባና የደረጃ እድገት፣ከፍትህ ተቋማት አሰራር፣ ፋይናንስ ነክ የሙስና ወንጀሎች እና ሀሰተኛ ሰነድ ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡

በተጨማሪም በመንግስት የኤሌክትሪክ፣ የፕሮጀክት ግንባታ፣ በገቢዎችና ጉሙሩክ አገልግሎት እንዲሁም በመልካም አስተዳደር እጦት ላይ የቀረቡ ጥቆማዎች እንዳሉበት ተገልጿል፡፡

በ7 ወራት ውስጥ ለኮሚሽኑ ከቀረቡ ጥቆማዎች ውስጥ ለፍትህ አካላት የተላኩ ጥቆማዎች ብዛት 175 መሆናቸውም ከኮሚሽኑ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያን
መጋቢት 09 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply