ቡርጂ እና አማሮ ልዩ ወረዳዎች በድርቅ የተጎዱ 150 ሺሕ ሰዎች ምግብ ይፈልጋሉ

https://gdb.voanews.com/01460000-0aff-0242-2d50-08da7199d880_w800_h450.jpg

በደቡብ ክልል ቡርጂ እና አማሮ ልዩ ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ከፍተኛ ድርቅ መከሰቱን ገልፀው ከብቶቻቸው በየቀኑ እየሞቱባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ በተከሰተው ድርቅ በሁለቱም ወረዳዎች ከ150 ሺሕ በላይ ዜጎች ለአስቸኳይ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን የወረዳው ባለሥልጣናት ገልፀዋል።

3.4 ሚሊዮን የክልሉ ነዋሪዎች ድጋፍ እንደሚፈልጉ በክልሉ የመንግሥት ቴሌቭዥን ጣቢያ ቀርበው ያስረዱት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ርስቱ ይርዳው በተለይ 2. 4 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች አፋጣኝ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል።

/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/

Source: Link to the Post

Leave a Reply