You are currently viewing ቡና ባንክ ለመምህራን እና ለጤና ባለሙያዎች ሲያካሄድ የቆየውን የይቆጥቡ ይሸለሙ መርሀ ግብር አጠናቆ አሸናፊዎቹን ይፋ አደረገ፡፡

ቡና ባንክ ለመምህራን እና ለጤና ባለሙያዎች ሲያካሄድ የቆየውን የይቆጥቡ ይሸለሙ መርሀ ግብር አጠናቆ አሸናፊዎቹን ይፋ አደረገ፡፡

ባንኩ ለ2ኛ ጊዜ ባዘጋጀዉ በዚህ ሽልማት፣ አንደኛ እጣ የ2021 ሞዴል ሱዙኪ ዲዛየር መኪና ፤ 12 ላፕቶፖች ፤ 12 ታብሌቶች ፤ 24 ስማርት ስልኮች እና 6 የጉብኝት ጥቅሎች ለባለድለኞች ተሰጥተዋል።

በዚህም መሰረት አንደኛ የአውቶሞቢል ሽልማት የሚያስገኝው የእጣ ቁጥር 4909927 ደጃች ውቤ ቅርንጫፍ ሆኖ ወጥቷል፡

ባንኩ የሀገር ባለውለታ ናቸው ያላቸው የሁለቱም ዘርፎች ባለሙያዎችን ለማበረታታትና የቁጠባ ባህል ለማዳበር ሲባል በሁሉም ደረጃ ያሉ መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች እንደተሳተፉበት ተገልጿል።

መርሐ ግብሩ 55 መምህራንና የጤና ባለሙያዎችን በአምስት የሽልማት ዘርፎች ከመኪና ጀምሮ ሙሉ ወጪው የተሸፈነ የሽርሽር ጉዞን ያካተተ ነው፡፡

ቡና ባንክ ከ12 አመታት በፊት የተቋቋመ ሲሆን 339 ቅርንጫፎች እንዳሉት ተገልጿል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 09 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply