ቡና ባንክ ለጤና ባለሞያዎች እና ለመምህራን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀው የሎተሪ እጣ በዛሬዉ እለት ወጥቷል፡፡የሎተሪ እጣዎቹ በብሄራዊ ሎተሪ በዕድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጡ ሲሆን የምእራብ መ…

ቡና ባንክ ለጤና ባለሞያዎች እና ለመምህራን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀው የሎተሪ እጣ በዛሬዉ እለት ወጥቷል፡፡

የሎተሪ እጣዎቹ በብሄራዊ ሎተሪ በዕድል አዳራሽ በህዝብ ፊት የወጡ ሲሆን የምእራብ መርካቶ ቅርንጫፍ ደንበኛ የሆኑት መምህር የ2020 ሞዴል ሱዙኪ ዲዛየር መኪና አሸናፊ መሆናቸዉ ታዉቋል፡፡

በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይም 12 ላፕቶፖች፣ 12 ዘመናዊ ታብሌቶች፣ 24 ስማርት የሞባይል ስልኮች እጣ ወጥቷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ 6 የእረፍት ጊዜ ሽርሽር ሙሉ ወጪ የተሸፈነላቸው የታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት ፓኬጆች ለእድለኞች ደርሰዋል፡፡

የቡና ባንክ ስትራቴጂ ዋና ኦፊሰር አቶ መንክር ሃይሉ እንዳሉት፣የመምህራን እና የጤና ባለሞያዎች የመጀመሪያው ዙር ፕሮግራም የሃገር ባለውለታዎችን ለማስታወስና የቁጠባ ባህልን ለማዳበር ታልሞ መዘጋጀቱን ገልጸዉ በሁሉም ደረጃ ላይ የሚገኙ መምህራን እና የጤና ባለሙያዎችን ተሳታፊ ያደረገ የቁጠባ መርሃ ግብር መሆኑን አስታዉሰዋል፡፡

ለአንድ ሀገርና ብልጽግና የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አቶ መንክር እነዚህ የሃገር ባለውለታዎች የቁጠባ ባህላቸውን ከማዳበርም በተጨማሪ ተሸላሚ የሚሆኑበትን አሰራር ቡና ባንክ መዘርጋቱን ገልጸዋል፡፡

ቡና ባንክ አ.ማ ከተመሰረተ 12 ዓመታትን ያስቀጠረ ሲሆን ከ311 በላይ ቅርንጫፎች እንዳሉት ከባንኩ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
መስከረም 11 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply