ቡና ባንክ ለ7ኛው ዙር የትራንስፖርት ዘርፍ ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር አሸናፊ ለሆኑ ደንበኞች ሽልማታቸውን በዛሬው እለት አስረክቧል፡፡ወ/ሮ ሄለን በቀለ የዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል አሸናፊ…

ቡና ባንክ ለ7ኛው ዙር የትራንስፖርት ዘርፍ ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር አሸናፊ ለሆኑ ደንበኞች ሽልማታቸውን በዛሬው እለት አስረክቧል፡፡

ወ/ሮ ሄለን በቀለ የዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል አሸናፊ ሲሆኑ ሌሎች አሸናፊዎችም ሽልማታቸውን ተረክበዋል፡፡

በባንኩ ዋና መ/ቤት በተካሄደው በዚሁ የሽልማት አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ አሸናፊ ለሆኑት ባለዕድለኞች፥ የአውቶሞቢል፣ የባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ፣ የሪፍሪጅሬተሮች፣ የዘመናዊ ስልኮች ፣ የፍላት ስክሪን ቴሌቪዥኖች፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች እና የውሃ ማጣሪያ ሽልማቶችን ማበርከቱን ባንኩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫው አመልክቷል።

ቡና ባንክ የጎላ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሚና ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ በማተኮር ባዘጋጀው በዚህ የቁጠባ እና ሽልማት ፕሮግራም፣ ዜጎች የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ የቁጠባ ባህልን ከማሳደግ በተጓዳኝ፣ የትራንስፖርት ዘርፍ ተዋንያንን በልዩ ሁኔታ በማበረታታት ገንዘባቸውን ቆጥበው ተሸላሚ እንዲሆኑ የሚያደርጋቸውን መርሃ ግብር በማዘጋጀት በትራንስፖርት ዘርፍ ለተሰማሩ ደንበኞቹ አጋር ሆኖ መቆሙንም ገልጿል፡፡

የሽልማት መርሃ-ግብሩ በማንኛውም ቀላልና ከባድ የፈሳሽ እና ደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ፣ መደበኛ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ‘ሚኒባሶች’፣ ‘ሚድ ባሶች’፣ ‘ሜትር ታክሲዎች’፣ ‘ባለሶስት እግር ታክሲዎች’ እንዲሁም የመካከለኛ እና ከፍተኛ ሃገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶች ላይ የተሰማሩ ባለንብረቶች፣ አሽከርካሪዎች ረዳቶች እና ትኬት ቆራጮችን ጨምሮ በዘርፉ ውስጥ የሚሰሩ ደንበኞች በዚህ የቁጠባና ሽልማት መርሃ ግብር ተሳታፊ ሆነዋል።

ባንኩ በዛሬው የሽልማት መርሃ ግብር ለአንደኛ ዕጣ ዘመናዊ ሱዙኪ ዲዛየር የቤት አውቶሞቢል፣ ለሁለተኛ ዕጣ አንድ የባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ፣ ሶስተኛ ዕጣ አራት ፍላት ስክሪን ቴሌቪዠኖች፣ አራተኛ ዕጣ አራት ሪፍሬጅሬተሮች፣ አምስተኛ ዕጣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖች፣ ስድስተኛ ዕጣ አራት የውሃ ማጣሪያዎች፣ እና ሰባተኛ ዕጣ አስር ዘመናዊ ሞባይል ቀፎዎችን ለባለዕድለኞች በዛሬው ዕለት አስረክቧል።

የገንዘብ ቁጠባ የግለሰቦችን ኑሮ ከመለወጥ ባለፈ ለምጣኔ-ሐብት ግንባታ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው የገለጸው ባንኩ፣ ህብረተሰቡ የዳበረ የቁጠባ ባህል እንዲያሳድግ ለማድረግ ቡና ባንክ የበኩሉን ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኝም ነው ገለጸው፡፡

በዚህም በየጊዜው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ የሚያደርጉ አዳዲስ የቁጠባ ፕሮዳክቶችን በመቅረጽና ማበረታቻ ሽልማቶችን በማዘጋጀት ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የማህበረሰብ ክፍል የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉንም ጨምሮ ገልጿል።

የ11ኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ መርሃ ግብር በሂደት ላይ ይገኛል ያለው ባንኩ፣ በቅርቡ ሲጠናቀቅ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በሚከናወን ይፋዊ ዕጣ የማውጣት ስነ-ስርዓት አሸናፊዎቹ የሚለዩ ይሆናል ነው ያለው፡፡
በተጨማሪም 8ኛው ዙር በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ ደንበኞች ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብርም በቅርቡ እንደሚጀመርም አስታውቋል፡፡

ከተመሰረተ 13 ዓመታትን ያስቆጠረው ቡና ባንክ፣ ከ14ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች ሲኖሩት ባንኩ በአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ ከ464 በላይ ቅርንጫፎች እንዳሉት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply