ቡና ባንክ በ3ኛው ዙር የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች ይቆጥቡ ይሸለሙ መርኀ ግብሩ ለባለዕድለኞች ሽልማቱን አስረከበ

ባንኩ በዘሬዉ ዕለት ባካሄደዉ የሽልማት መርሃ ግብር አሸናፊ ዕድለኞች የአውቶሞቢል፣ ላኘቶኘ፣ ታብሌት፣ እና ዘመናዊ የሞባይል ቀፎ ሽልማቶችን ተረክበዋል ።

ቡና ባንክ መምህራንና የጤና ባለሙያዎች ላሳዩት የቁጠባ ጥረት አሸናፊ የሆኑ ዕድለኞችን ነዉ የሸለመዉ፡፡

ባንኩ የቁጠባ ባህልን ለማስፋፋት በመሰል መርሃ ግብሮች ትኩረት ሰርቶ እንደሚሰራ አስታዉቋል ።

ህብረተሰቡ ቁጠባን ባህል በማድረግ የይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃግብሮች ላይ እንዲሳተፍ በባንኩ አመራሮች ጥሪ ቀርቧል፡፡

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ሶስተኛ ትዉልድ ሀገር በቀል ተቋም እንደሆነ የገለጸዉ ቡና ባንክ ከ 2 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን እያገልገለ ነዉ ተብሏል፡፡

ባንኩ አዳዲስ የፋይናንስ አካታችነትን በማስተዋወቅ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም ተነስቷል፡፡

አባቱ መረቀ
ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply