ቡና ባንክ የእጣ አሸናፊ ደንበኞችን ይፋ አደረገ፡፡

ባንኩ በአስረኛው ዙር የውጪ ገንዘብ ይቀበሉ፣ይመንዝሩ እና ይሸለሙ መርሃ-ግብር ባዘጋጀው እጣ 30 ደንበኞችን ተሸላሚ አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል አሸናፊ እጣ ቁጥር 0040979 ሆኖ ወጥቷል፡፡

ሁለተኛው ቴሌቭዢን አሸላሚ ያደረገው የእጣ ቁጥር ደግሞ 0016505 በመሆን የወጣ ሲሆን፣ በሶስተኛ ደረጃ የልብስ ማጠቢያ ማሽን ያሸለመው የእጣ ቁጥር 0012644 መሆኑ ታውቋል፡፡

ባንኩ ጥቁር ገበያ በኢኮኖሚው ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ ለመከላከል በማቀድ የዉጪ ገንዘብ በህጋዊ መንገድ መመንዘርን ለማበረታታት ባለፉት 12 ዙሮች ደንበኞችን እየሸለመ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ወደ ሃገር ከሚመጣው የውጪ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛው ከመደበኛ የባንክ አገልግሎት ይልቅ በተለያዬ ምክንያት በጥቁር ገበያ የሚገባ ነው ተብሏል፡፡
ይህም ሃገራችን በተደጋጋሚ ለሚገጥማት የውጪ ምንዛሬ እጥረት እንደ ዋና ምክንያት ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሰኔ 23 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply