ቡና ባንክ የ11ኛው ዙር የውጭ ምንዛሬ ደንበኞች ይቀበሉ ፣ ይመንዝሩ ይሸልሙ የሽልማት መርሃ-ግብር አሸናፊዎች በዛሬው እለት ይፋ ተደርጓል፡፡የባንኩ የዘንድሮው የውጭ ምንዛሬ ደንበኞች ይቀበሉ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/a7lGfObec5qG9nkCGOHD7_72DGdR9sLb-N-MYJX3NC9qzrVItCFhjsWynK_gSUOrwqsmBMDh0q4TOWGeTLAiqIyWBjEUbFpk4UUqGj-NSFWlNTb9aXJHR0e1ALAU-NZfchWI2mjhcG5ujrm2MZnIAajCBjSS3MRpSOxw_-x5QRNxZQ_jB8__dTZTOYZe7C_QPIIyqhTOGP7RXcvXMMaUIIYcBLtQY-OZvCae2WNEYNDCEZjrZ9-qOOESDPwHtWyp3lF1AEd12R2kx-xuImn8mdm6uTlF36Km-ZgGxNxV3x6vqvdRhYccNvb7kMKWQnyEH9QgBoTOwC3APB-7i5hC0w.jpg

ቡና ባንክ የ11ኛው ዙር የውጭ ምንዛሬ ደንበኞች ይቀበሉ ፣ ይመንዝሩ ይሸልሙ የሽልማት መርሃ-ግብር አሸናፊዎች በዛሬው እለት ይፋ ተደርጓል፡፡

የባንኩ የዘንድሮው የውጭ ምንዛሬ ደንበኞች ይቀበሉ ፣ይመንዝሩ ይሸለሙ የሽልማት መርሃ-ግብር አሸናፊዎች የተለዩ ሲሆን በዚህም መሰረት ወ/ሮ ጌጤ አባይነህ የዘመናዊ የቤት መኪና አውቶሞቢል አንደኛ እጣ ተሸላሚ ሆነዋል።

የሁለተኛ እጣ ዘመናዊ ማቀዝቀዣ ተሸላሚ የሆኑት እስጢፋኖስ በለጠ እና አጋዤ መኮንን ሲሆኑ የሶስተኛ እጣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን ተሸላሚ የሆኑት ደግሞ አቶ ታከለ ብርሃኑ እና ብርሃን ያዝን ናቸው፡፡

እንዲሁም የ4ኛ እጣ የውሃ ማጣሪያ ተሸላሚ ጽጌ አደራ እና ወ/ሮ ብዙነሽ ጌታነህ ሲሆኑ በተጨማሪም የ5ኛ እጣ አሸናፊዎች ዘመናዊ ስልክ ተሸልመዋል፡፡

ባንኩ የ11ኛው ዙር የውጭ ምንዛሬ ደንበኞች ይቀበሉ ፣ ይመንዝሩ ይሸልሙ የሽልማት መርሃግብር በዚህ መልኩ ያከናወነ ሲሆን የ12ኛውን ዙር የሽልማት መርሃ ግብርም በቅርቡ ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይም ባንኩ የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ በማዘመን ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ እየተጋ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply