ቡና ባንክ 2022/2023 የበጀት ዓመትን እንዴት አሳለፈ ከግብር በፊት 1 ነጥብ 35 ቢሊዮን ብር አትርፏል የባንኩ አጠቃላይ ሃብት 46 ነጥብ 39 ቢሊዮን ብር ደርሷል ለልማትና በ…

ቡና ባንክ 2022/2023 የበጀት ዓመትን እንዴት አሳለፈ

 ከግብር በፊት 1 ነጥብ 35 ቢሊዮን ብር አትርፏል
 የባንኩ አጠቃላይ ሃብት 46 ነጥብ 39 ቢሊዮን ብር ደርሷል
 ለልማትና በጎ አድራጎት ተግባራት የ41 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል

ቡና ባንክ አ.ማ ዓመታዊውን የባለአክሲዮኖች 14ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በቀን 30/03/16 አካሂዶ ነበር፡፡

በርካታ ቁጥር ያላቸው ባለአክሲዮኖች በታደሙበት በዚህ ጉባኤ የቡና ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አምባሳደር ዓለምአየሁ ሰዋገኝ የባንኩን የ2022/2023 ዓመታዊ ሪፖርት አቅርበው ነበር፡፡
በሪፖርቱ እንደተገለጸው፤

• ባንኩ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ከግብር በፊት 1.35 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዝግቧል፤ከ36.59 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ ችሏል፡፡

• እ.ኤ.አ ሰኔ 30 በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ካለፈው ዓመት በ9.4 ቢሊዮን ብር ማሳደግ ተችሏል፤አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በ34.6 በመቶ ከፍ በማድረግ 36.6 ቢሊዮን ብር ደርሷል፤የቁጠባ ሂሳብ ተቀማጭ 73.3 በመቶ የሚሆነውን ከፍተኛ ድርሻ መያዙ ተነግሯል፡፡

• ባንኩ በዓመቱ ውስጥ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በአጠቃላይ 8.92 ቢሊዮን ብር አበድሯል፤ይህም ባንኩ በአጠቃላይ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ያበደረውን የገንዘብ መጠን በ34.5 በመቶ በማሳደግ 34.78 ቢሊዮን ብር አድርሶታል፡፡

• የባንኩ የውጭ ምንዛሬ ግኝት 175.7 ሚሊዮን የሚጠጋ የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የወጭ ንግድ 55.5 በመቶ የሚሆነውን በመሸፈን ቀዳሚ መሆኑን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡ባንኩ የውጭ ሃገር ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ጋርም የቀጥታ ግንኙነት መስርቶ በመስራት ላይ ይገኛል ነው የተባለው፡፡

• የባንኩ ጠቅላላ ሃብት በበጀት ዓመቱ 12.29 ቢሊዮን ብር እድገት በማሳየት 46.39 ቢሊዮን ብር ደርሷል፤የባንኩ ካፒታል በበጀት ዓመቱ የብር 1.5 ቢሊዮን ብር እድገት ያሳዬ ሲሆን ይህም የባንኩ አጠቃላይ የካቲታል መጠን 6.5 ቢሊዮን ብር አድርሶታል፡፡

• ባንኩ በበጀት ዓመቱ 122 አዳዲስ ቅርንጫፎችን የከፈተ ሲሆን ይህም እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ የከፈታቸውን የቅርንጫፎች ብዛት 465 አድርሶታል፤የደንበኞች ቁጥርም ከ 3 ሚሊዮን ተሻግሯል፡፡

የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎትን በተመለከተ

• በ2022/2023 በጀት ዓመት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ የባንክ ቅርንጫፎች፣ሆቴሎች፣እንዲሁም የንግድ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ላይ የተተከሉ የገንዘብ መትከያ ማሽኖች ቁጥር 194 ደርሷል፡፡

የአዳዲስ ካርድ ተጠቃሚዎች ቁጥር 171 ሺህ አካባቢ ተጠግቷል፤የባንኩ አጠቃላይ የካርድ ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር 371 ሺህ 021 ደርሷል፤በባንኩ የገንዘብ መክፈያ ማሽኖች 1.8 ቢሊዮን ብር ማንቀሳቀስ ተችሏል፤የሞባይልና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር ያደገ ሲሆን በዚህም በድምሩ 10.6 ቢሊዮን ብር በላይ ገምዘብ ልውውጥ መደረጉን ሪፖርቱ ዓመልክቷል፡፡

• ባንኩ በበጀት ዓመቱ በድምሩ 41.8 ሚሊዮን ብር ለማህበራዊ ድጋፍ፣ለአካባቢ ተኮር ፕሮጀክቶችና ለሌሎች ግብረ-ሰናይ ተግባራት እንዲውል ድጋፍ ማድረጉም በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

• ቡና ባንክ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለምዶ ሰንጋ ተራ በሚባለው አካባቢ በተረከበው 1043 ስኩየር ሜትር ስፋት ባለው ቦታ ከምድር በታች 3 ወለል እና ከምድር በላይ 23 ወለሎች ያሉት ሁለገብ ህንጻ ለመገንባት ከስራ ተቋራጭ ጋር ውል አስሯል፡፡

በተለምዶ ዲ አፍሪክ በሚባለው አካባቢ ደግሞ ለባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የህንጻ ግንባታ አገልግሎት የሚውል 4 ሺህ 530 ካሬ ሜትር መሬት በሊዝ ይዞታ የባለቤትነት መብት ለመረከብ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

ከተመሰረተ 14 ዓመታትን ያስቆጠረው ቡና ባንክ ከ13 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖችና ከ 4 ሺህ በላይ ሰራተኞች እንዳሉት በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ
መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8)

Source: Link to the Post

Leave a Reply