ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በ2019/20 በጀት ዓመት ከግማሽ ቢሊዮን በላይ ብር ማትረፉን አስታወቀ። ባንኩ 11ኛ የባለአክስዮኖች ጉባኤውን በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል። የባንኩ ሊቀመን…

https://cdn4.telesco.pe/file/dj0klFnc7BOLnLJGc2_UdmpVUyE99GZGvHRBFH7IX9yVnmP-yevOx2BT5iOrVBho6xDJfP7apJcyupVxwne_fw3A0pME_m-vpg6H_N2GbKDWfjknVOiEkR96dDzDibyXQHMSguMfgvl7ojfsD4HPjYnZRnPI6jE_rkjjScWhId80gq-wmbD4pFrADFbsGHdj0VZRshJ2s9r5d3gL5miQ6qbBDGRDfp6pC3Ih9FTcorU_dmBc1BhtOdzUUww9jyyti_I2mojN6ddVBEP9CV84q7KM8A6H0aA5bBdbrzVV8IFwHim8SlKIMdAyARPOrXatv1X0QrHhGZ8mEGKiz0hkQQ.jpg

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ በ2019/20 በጀት ዓመት ከግማሽ ቢሊዮን በላይ ብር ማትረፉን አስታወቀ።

ባንኩ 11ኛ የባለአክስዮኖች ጉባኤውን በአዲስ አበባ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የባንኩ ሊቀመንበር ዶክተር ሰውአለ አባተ በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ባንኩ እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ 2019/20 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን ከታክስ በፊት 582 ሚሊዮን ብር ትርፍ አግኝቷል።

ባንኩ በተያዘው ዓመት ያስመዘገበው ትርፍ ባሳለፍነው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ43 ሚሊዮን ብር ገደማ ቅናሽ ማሳየቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከባንኩ ዓመታዊ ሪፖርት ተረድቷል።

ባንኩ ለደንበኞቹ ያበደረው መጠን እስከያዝነው በጀት ዓመት ድረስ 11 ነጥብ 57 ቢሊዬን ብር የደረሰ ሲሆን የወጪ እና ገቢ ንግድ፣ ኮንስትራክሽን ፣ የአገልግሎት ዘርፍ እና የአገር ውስጥ ንግዶች ባንኩ ብድር የሰጠባቸው የስራ ዘርፎች ናቸው።

የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ መጠን አሁን ላይ 14 ቢሊዮን ገደማ ብር የደረሰ ሲሆን በተያዘው ዓመት 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን የባንኩ ዓመታዊ ሪፖርት ያስረዳል።

ባንኩ እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት 440 ነጥብ 3 ሚሊዮን የተጣራ ትርፍ ያገኘ ሲሆን 270 ሚሊዮን ብሩን ለባለአክስዮኖች እንደሚያከፋፍል ቀሪውን ብር ደግሞ ወደ መጠባበቂያ ቋቱ እንደሚያስገባ ገልጿል።

ከ11 ዓመት በፊት የተመሰረተው ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ 242 ቅርንጫፎች ፣810 ሺህ ገደማ ደንበኞች እንዲሁም 15 ሺህ ባለአክስዮኖች ያሉት የግል ባንክ ነው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል ድረ ገጻችንን https://ethiofm107.com/ ይጎብኙ::

ሳሙኤል አባተ
ታህሳስ 11 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply