ቡድኑ ሃገር ለማፍረስ የሚጠቀመው የጭካኔ ስነ ልቦና የትግራይን ህዝብ አይወክልም !! አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-14/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር በሮም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የህወ…

ቡድኑ ሃገር ለማፍረስ የሚጠቀመው የጭካኔ ስነ ልቦና የትግራይን ህዝብ አይወክልም !! አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-14/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር በሮም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የህወ…

ቡድኑ ሃገር ለማፍረስ የሚጠቀመው የጭካኔ ስነ ልቦና የትግራይን ህዝብ አይወክልም !! አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-14/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር በሮም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የህወሃት ጁንታ ለህዝብና ለሃገር ሲል እጁን እንዲሰጥ ጠየቁ። በጣሊያን ሮም አደባባይ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በህወሃት ጁንታ ለተጨፈጨፉ ወገኖች የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት እና ህግን በማስከበር ላይ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል። ሰልፉ በሃይማኖት አባቶች ፀሎት የጀመረ ሲሆን ከአገራችን ኢትዮጵያ ጠላቶቿን በማሳፈር ዘመን አይሽሬ ታሪኮችን ያስመዘገበችው አባቶቻችን በአንድነት እንደሆነ አስታውሰው አሁን ቡድኑ የሰራው በአገራችን ታሪክ ታይቶ የማያውቅ የጭካኔ ስራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ መንግስት ህዝብን ከችግር እንዲታደግ፣ አጥፊዎችን ወደ ህግ እንዲያቀርብ እና የአገራችንን አንድነት እንዲያስጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል። የተለያዩ ተሳታፊዎች ህወሃት አገር ሲያስተዳድር በነበረበት ወቅት በአገር ላይ ያደረሰውን በደል፣ በመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ላይ ያደረሰውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ እንዲሁም አሁንም በቀረው የስዓት ሽርፋራፊ ዕድሜ በአገር እና ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን በደል፣ የቡድኑ ስሪት በክፋት ለክፋት ስለሆነ በጥንቃቄ መወገድ እንዳለበት ማሳሰባቸውን በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል። የሰልፉ ተሳታፊዎች ህወሃት አገሪቱን ለማበጣበጥ የፅንፈኛ ቡድኖችን በማሰባሰብ እና ስፖንስር በማድረግ ንፁሃንን ያስጨፈጭፍ እንደነበር አንስተዋል። የመንግስትን ሆደ ሰፊንትን ካቅም ማነስ በመቁጠር በጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በታሪክ አሳፋሪውን እና ዘግናኙን ተግባር አብረውት በኖሩት የሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ መፈፀሙን ገልጸዋል። ቡድኑ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት እና አገር ለማፍረስ የሚጠቀመው የጭካኔ ስነ ልቦና ግራ ቢያጋባም የትግራይን ህዝብን ግን እንደማይወክል ተናግረዋል። መንግስት እነዚህን ወንጀለኖች ለህግ ማቅረብ እና አካባቢውን ማረጋጋት እንዳለበት ለዚህም መንግስት ለሚያከናውነው የህግ ማስከበር እንቅስቃሴ እና ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታት ለሚያደርገው ተጋድሎ ከፍተኛ አድናቆት እና ድጋፍ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል። በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ እስካሁን የሰራኸውን ስህተት፣ እየፈሰሰ ያለውን ደም እና እየወደመ ያለውን የአገር ንብረት እንዲሁም የመያዛችሁን አይቀሬነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ያለ ተጨማሪ ጥፋት እጃችሁን ስጡ የሚል ጥሪ ለህወሃት ጁንታ ቡድን አቅርበዋል። ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply