
ቡፎን እስከ 46 ዓመቱ መጫወቱን ይቀጥላል
የቀድሞው የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ጂያንልዊጂ ቡፎን በፓርማ ኮንትራቱን እስከ 2024 አራዝሟል፡፡
የ44 ዓመቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ በሴሪ ቢ የሚጫወተውን ክለብ በሁለት ዓመት ኮንትራት በድጋሜ የተቀላቀለው ባለፈው ክረምት እንደነበር ይታወሳል፡፡
ቡፎን ከጁቬንቱስ ጋር አስር የሴሪ አ ዋንጫዎችን አሸንፏል ፤ በጣሊያን ሴሪ አ 657 ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ በቀዳሚነት ክብረ ወሰን ጨብጧል፡፡
‹‹ ለእኔም ሆነ ለቤተሰቦቼ አስደሳች ቀን ነው ፤ ከተማዋ እና ደጋፊዎቿ ደስተኛ እንደሚሆኑም ተስፋ አደርጋለሁ ›› ብሏል ፡፡
አቤል ጀቤሳ
የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም
Source: Link to the Post