ቢሮው በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የህብራት ሥራ ማህበራት የ22 ሚሊየን ብር የኦዲት ጉድለት መገኘቱን አስታወቀ

ሰኞ ሰኔ 27 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ የህብራት ሥራ ማህበራት የ22 ሚሊየን ብር የኦዲት ጉድለት መገኘቱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አደም ኑሪ ተናገሩ።

በህብረት ሥራ ማህበራት እንቅስቃሴና ያሉባቸውን ችግሮች መቅረፍ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ሲሆን፤ ማህበራቱ ለህብረተሰቡ አሥፈላጊውን አገልግሎት መሥጠት እንዲችሉ ህግን አክብረው እንዲሰሩ ማድረግ እንደሚገባም የቢሮ ኃላፊው አስገንዝበዋል።

በመዲናዋ በተለያዩ ዘርፎች የተደራጁና ኃላፊነት የተጣለባቸው የህብረት ሥራ ማህበራት ያሉባቸውን ችግሮች በመቅረፍ ረገድ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው ያሉት የንግድ ቢሮ ኃላፊው አደም ኑሪ፤ የበለጠ ለማጠናከር የፍትህ ተቋማትና ባለድርሻ አካላትም በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

በማህበራቱ ዘንድ እስካሁን ባለው ሂደት ከ22 ሚሊየን ብር በላይ የኦዲት ጉድለት መገኘቱን ያነሱት አደም፤ ከዚህ ውስጥ 7 ሚሊየን ብር ተመላሽ መደረጉንና በቀጣይም ብክነት ያስከተሉ አካላትን ተጠያቂ እንደሚሆኑ ገልፀዋል።

በመዲናዋ ከ9 ሺህ 300 በላይ የተለያዩ የህብረት ሥራ ማህበራት በሥራ ላይ መሆናቸውን የገለጹት የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው አሊ በበኩላቸው፤ የሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት በምርት አቅርቦት፣ የቁጠባ እና ብድር የህብረት ሥራ ማህበራት በሥራ እድል ፈጠራ የተሻለ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን መናገራቸውን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል።

በአዲስ አበባ ከተማ 148 የሽማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት እንዲሁም 6 ሺህ 19 የቤቶች ህብረት ሥራ ማህበራትን ጨምሮ በሌሎች ዝርፎችም የተደራጁ የህብረት ሥራ ማህበራት ከ5 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚያንቀሳቅሱ ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply