ቢሮው ተጨማሪ 2 የነዳጅ ቦቴዎችን በዛሬው ዕለት መውረሱን አስታወቀ

ማክሰኞ ሰኔ 28 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ የነዳጅ እጥረት እንዲከሰትና ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ በመጣስ ከህግ ውጪ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ወደ ከተማ እንዳይገቡ የተደረጉ፤ ተጨማሪ 2 የነዳጅ ቦቴዎችን በዛሬው እለት በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ጥቆማ በውረስ የጫኑት ነዳጅ በነዳጅ ማደያዎች በኩል እንዲከፋፈል ማድረጉን አስታውቋል።

የንግድ ቢሮ ም/ሃላፊ መስፍን አሰፋ ይህንን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ በዛሬው ዕለት ተጨማሪ 2 የነዳጅ ቦቴዎች ተደብቀው በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ትብብር የተያዙ ሲሆን የጫኑት ከ 80 ሺህ ሊትር በላይ የሚገመት ነዳጅ በማደያዎች በኩል መከፋፈሉን ገልጸዋል።

እስከ አሁን ድረስ ቢሮው በወሰደው እርምጃ 12 የነዳጅ ቦቴዎችን ወርሶ የያዙትም ነዳጅ በማደያዎች በኩል ለተጠቃሚዎች መከፋፈሉን አብራርተው፤ ህግ አክብረው በማይሰሩና ሆን ብለው እጥረቱ እንዲባባስ በሚያደርጉ የነዳጅ ካምፓኒዎች ላይ አሁንም እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሃላፊው መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply