ቢያንስ የቀጠሮ ለቅሶ እንኳን በየአካባቢው እንዲደረግላቸው ተጠየቀ፡፡ (አሻራ ጥር 9፣ 2013 ዓ.ም)  በመተከል በጫካ በመንግስት ትዕዛዝ የተቀበሩ ንፁሃን ቢያንስ በየአካባቢው የቀጠሮ ለቅሶ…

ቢያንስ የቀጠሮ ለቅሶ እንኳን በየአካባቢው እንዲደረግላቸው ተጠየቀ፡፡ (አሻራ ጥር 9፣ 2013 ዓ.ም) በመተከል በጫካ በመንግስት ትዕዛዝ የተቀበሩ ንፁሃን ቢያንስ በየአካባቢው የቀጠሮ ለቅሶ…

ቢያንስ የቀጠሮ ለቅሶ እንኳን በየአካባቢው እንዲደረግላቸው ተጠየቀ፡፡ (አሻራ ጥር 9፣ 2013 ዓ.ም) በመተከል በጫካ በመንግስት ትዕዛዝ የተቀበሩ ንፁሃን ቢያንስ በየአካባቢው የቀጠሮ ለቅሶ ተደርጎላቸው በስራዓት እንዲቀበሩ ጠየቀ፡፡… አስተያያታቸውን ለአሻራ የሰጡ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች በመተከል የሚደረገው ዘግናኝ ጭፍጨፋ መንግስት ማዳን ባለመቻሉ ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡ ከተራ እንስሳት ባነሰ ክብር አስከሬናቸው በጫካ መደፈቱም አሳዝኗቸዋል፡፡ የሰው ልጅ ሲጨፈጨፍ ዝምታን የመረጡ የመንግስት አካላት እንዲጠየቁ ወጣቶችም በአንድ በኩል እየጠየቁ ሲሆን፣የአዊ እና ባህርዳር የሀገር ሽማግሌዎች ደግሞ የቀጠሮ ለቅሶ እንዲደረግላቸው እናደርጋለን እያሉ ነው፡፡ የሀይማኖት አባቶችም እንደየ ሀይማኖታቸው ስራዓት ቀብራቸው እንኳን እንዲፈፀም ጠይቀዋል፡፡ መንግስት ግን በማስጨፍጨፍ፣ ጭፍጨፋውንም በመካድ፣ የተጨፈጨፉትም በጫካ እንዲወቅድ በማድረግ እየተከሰሰ ነው፡፡ የምክርቤት አባላትም የሀዘን ቀን አለማወጃቸው እና በጉዳዮ ዙሪያ ትኩረት አለማሳየታቸው እያነጋገረ ነው፡፡ መንግስት የማዳንም፣ አስጨፍጭፎም ለአስከሬን እንኳን ክብር በመንሳቱ እኛ ጭፍጨፋው እንዲቆም የትኛውንም አዋጭ ስራ እንሰራለን የሚሉ ድምፆች እየተሰሙ ሲሆን፣ የሀይማኖት አባቶች እና ሽማግሌዎች ግን በተደራጀ እና ባህሉ በሚፈቅደው ሁኔታ የቀጠሮ ለቅሶ ለማድረግ ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply