ቢጂአይ ኢትዮጵያ ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን ለማዘመን ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ አውጥቻለሁ አለ።በጥር 2015 ከንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ቢጂአይ ኢትዮጵያ ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን ከራ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/EmaOG4sV0Xhppbxr4xJCJZpnfHyBhk3bbkppXTMFjqg7Tom20Zb9L1KMa51nfk56F-IFE08NDEE4cE8Ku24A4EdDlAyFF2Zk18CTkKW-ghzQshx0aFty_x_sL5Wz_8IVvx76GStdW5fyReLiWXlNoHrM6MdEEXZvqD_7DYNcjGePtLB0D3LodqJuxY_z2MQ0k32jmTHTmm8uIco1P-ar1OxE3gupW8SVcQa2MrM-tIH_NDezXSBcOhNhOvb1IbP2S59FG0px6smhlsiJFcILpzGwryBxSYdcdhgHNgmTrhSKL66YKRPG5ui5utokDVIyb7xMSOmutFfXXPk6WQfm-w.jpg

ቢጂአይ ኢትዮጵያ ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን ለማዘመን ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ አውጥቻለሁ አለ።

በጥር 2015 ከንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ቢጂአይ ኢትዮጵያ ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን ከራሱ ጋር ለማዋሃድ የሚያስችለውን ፍቃድ ማግኘቱ ይታወሳል።
በዚህም ቢጂአይ ኢትዮጵያ ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን ለማዘመንም ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጉ ነው የተገለፀው።

ቢጂአይ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን እንደገና ለማደስና ለማስፋፋት ከ550 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ አድርጌያለሁ ነው ያለው።

የቢጂአይ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሄርቬ ሚልሃድ በሰበታ ከተማ በሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ከ10 ወር በፊት የቢራ ፋብሪካውን መገዛቱን አስታውሰው ፣ በእነዚህ ወራትም የፋብሪካውን አቅም ለማሳደግ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።

ሜታ አቦን በወር 3 መቶ ሺህ ሄክቶ ሊትር ለማምረት የሚችልና ከቢጂአይ ቤተሰብ ድርጅቶች ውስጥ ትልቁ የቢራ ፋብሪካ ለማድረግ በማቀድ አስፈላጊው ስራ መሰራቱንም ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለዋል።

ከዚህም ባሻገር ቢጂአይ የእድሳትና የማስፋፋት ሥራውን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሰበታ አከባቢ ለሚገኙ 1ሺህ 5 መቶ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል ተብሏል።

በእስከዳር ግርማ
የካቲት 10 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply