ባህላዊ ልብሳችን እንድንቀይር እየተገደድን ነው—የዶንጋ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የዶንጋ ብሔረሰብ የባህል ልብስ ለመቀየር በሀላፊዎችና በግለሰቦች ደረጃ የሚደረግ ሙከራ በአስቸኳይ እንዲቆ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/SzgIJCoHdwCAEDHIFP6xfVp2vp4DBV6UzRXyCi49mAs23uqaLcddU9Y198Ve6Iz8ggv7NCXr4zI7467LLXvcbz7crjFZzP_RS8r1YU7208DFMVlQEhkPgEKduq3Scah3nsSZ4eluVOrMvVyzURDDkY6mGNh29Yv_KGrjuKL90fzaKDFTRmlE-KXQOOgQYfpIM9swTZiEXhZmP5xDloxfWxmdLKfukL8y1_Rwx9XVcaq9Sd90tHmCVRZDtcENoQvSb8_IP8ERP1txJYrKR0GYbyfFqT7JOOGAy1lPhLl0xuPjQObshjz5s_FXK9IITOSvqonlzgi1hlHfrTHIMp6VEQ.jpg

ባህላዊ ልብሳችን እንድንቀይር እየተገደድን ነው—የዶንጋ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ

የዶንጋ ብሔረሰብ የባህል ልብስ ለመቀየር በሀላፊዎችና በግለሰቦች ደረጃ የሚደረግ ሙከራ በአስቸኳይ እንዲቆም ፓርቲው ገልጿል።

ነባሩን የዶንጋን ብሔረሰብ ባህል ልብስ ለመቀየር ጥረት ማድረግ ለብሔረሰቡ ጥቅም ታስቦ ሳይሆን የሌላ የፓለቲካ አጀንዳ ያለዉ መሆኑን ነው ፓርቲው የገለጸው።

ስለሆነም የዶንጋ ብሔረሰብ ባህላዊ አስተዳደር ሥርዓት ፤ ምሁራንና ሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች እዉቅና ውጭ፣ በባህል ልብስ ላይ ለዉጥ ለማድረግ መሞከር ህዝብን መናቅና ዶንጋ ምሁር እንደሌለ ከማሰብ ባለፈ ህገ-መንግስታዊ መብታችንን የመቃወም አጀንዳ የያዘ ህገ-ወጥ ተግባር ነዉ ብሏል።

የዶንጋ ህዝብ መብቴ ይረጋገጥ በማለቱ ለመከራ እየተዳረገ ነው ሲልም የዶንጋ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታውቋል።

ፓርቲው የክልሉ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ ወደ ጎን በማለቱ የፌደራል መንግስት ለዶንጋ ህዝብ ይድረስለት ሲልም ጠይቋል።

የዶንጋ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ የሚያቀርቡ ዜጎች ለእስር ተዳርገው እንግልት እና መከራ እየደረሰባቸው ሲል ፓርቲው አስታውቋል።

ከህግ አግባብ ውጪ የዶንጋ ህዝብ ባህሉን እንዲጥል ባህላዊ ልብሱን እንዲቀይር እየተገደደ ይገኛልም ነው ያለው ፓርቲው።

ፓርቲው በዶንጋን ህዝብ ጥያቄ የከንባታ ዞን ጣልቃ እየገባ የህዝቡን ጥያቄ እያደናቀፈ ይገኛል ሲል ወቅሷል፡፡

ህገመንግስታዊ ጥያቄው አልተመለሰም ያለው ፓርቲው በዶንጋ ህዝብ ላይ ህገመንግስቱን የሚጻረር ተግባር እየተፈጸመበት ይገኛልም ብሏል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply