
#ባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ከ7 በላይ ቀበሌዎች የመኪና መንገድ ባለመኖር ምክንያት ለበርካታ አመታት እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ተገለፀ። የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በህርዳር ዙሪያ ወረዳ ከ7 በላይ ቀበሌዎች ለ20 አመታት መንገድ እንዲሰራላቸው ከተማ አስተዳድሩን ቢጠይቁም እስካሁን ድረስ መልስ እንዳላገኙ ገልፀው ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የየሞሽት ቀበሌ ነዋሪዎች ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል። ለህክምና እና ለግብይት አራት ሰአታትን ተጉዘው ባህርዳር ከተማ የሚደርሱት እነኚህ የቀበሌው ነዋሪዎች በየቀኑ በርካታ ነፍሰጡሮች እና ህምምተኞች መንገድ ካለማግኘታቸው የተነሳ ህዎታቸው እንደሚያልፍ ገልፀዋል። ህክምና ካለማግኘታቸው በተጨማሪ እለት ከዕለት ኑሯቸውን ለመምምራት እና ግብይት ለመፈፀም ባህርዳር ከተማ ለመድረስ ለአራት ሰዓታት ተጉዘው እንደሚደርሱ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ እንደገለፁት የፈረስ ጋሪ እንኳን የሚሆን መንገድ ካለመኖሩ የተነሳ ለምግብ ጤፍ ለማስፈጨት ሴቶች በወገባቸው ተሸክመው ለሰዓታት እንደሚጓዙ አብራርተዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post