ባለሀብቶች መዝናኛ ቦታዎችን እና ፖርኮችን እንዲያለሙ ጥሪ ቀረበላቸዉ። ጥሪዉን ያደረገዉ የአዲስአበባ መዝናኛ ቦታዎችና ፖርኮች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ነዉ። ኮርፖሬሽኑ የእንጦጦ ፖርክን ጨምሮ…

ባለሀብቶች መዝናኛ ቦታዎችን እና ፖርኮችን እንዲያለሙ ጥሪ ቀረበላቸዉ።

ጥሪዉን ያደረገዉ የአዲስአበባ መዝናኛ ቦታዎችና ፖርኮች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ነዉ።

ኮርፖሬሽኑ የእንጦጦ ፖርክን ጨምሮ 10 የሚሆኑ ፖርኮችን የሚያስተዳድር ሲሆን ብሄረ ፅጌ፣አምባሳደር ፖርክ፣ልደታ ፖርክ፣ፋና ፒኮክ ወይም አዲስ ዙ ፓርክ ፣ኢትዮ ኮሪያ፣ኢትዮ ኩባ ፣ከንቲባ ወልደፃዲቅ ፓርክ እና ሀምሌ 19 የመሰሉ ፖርኮች ይገኙበታል።

ከአስሩ ፖርኮችም ሶስት ፖርኮች ለባለሀብቶች የተከራዩ ሲሆን እነዚህም አምባሳደር ፖርክ፣ልደታ ፖርክ እና ከንቲባ ወልደፃዲቅ ፖርክ ናቸዉ።

በኮርፖሬሽኑ የኢኮ-ቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ተፈራ በ2016 ዓ.ም 1ሚሊዮን ጎብኚ ለማግኘት አቅደዉ በ10 ወራት ዉስጥ 800ሺህ ጎብኚዎች ማስተናገዳቸዉን ተናግረዋል።

ከነዚህ ጎብኚዎችም በያዝነዉ ዓመት ብቻ 70ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 87በመቶ ማሳካት መቻላቸዉን ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ቦታዎችና ፖርኮች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በ1.4 ቢሊየን ብር ካፒታል የተቋቋመ የልማት ድርጅት ሲሆን ከዚህ ዉሰጥ 827 ሚሊዮን የሚሆነዉ የተከፈለ ነዉ።

ቀሪዉ ገንዘብ እስከ 2018 ከከተማ አስተዳደሩ የሚከፈል መሆኑን የሚናገሩት አቶ ሙሉጌታ ይህ ድጎማ እስከ 2018 ብቻ ሲሆን ከዛ ወዲህ ኮርፖሬሽኑ እራሱን ይችላል ብለዋል።

ኮርፖሬሽኑ ከሚያስተዳድራቸው አስር ፖርኮች ዉስጥ አምስቱ መስፈርት የሚያሟሉ ሲሆኑ አምስት መስፈርት የማያሟሉ ናቸዉ ተብሏል ።

ከማያሟሉት አምስቱ ዉስጥም ሶስቱ ወደ ግንባታ ለመግባት ዲዛይናቸዉ በዚህ ዓመት ተጠናቋል ብለዋል።

በከተማዋ ከሚገኙት ትልቅ ፖርክች መካከል ወዳጅነት ፖርክ እና ዩኒቲ ፖርክ በፌደራል ደረጃ የሚተዳደሩ መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply