
ተደጋጋሚ ግጭት ባጋጠመው የአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ፍኖተ ሰላም ባለመረጋጋቱ እና ባለሙያዎች ደረሰብን ባሉት ጫና ምክንያት ከተማዋ ያለ ሆስፒታል ሥራ ማቆሙ ተነገረ። ሥራ በመቆሙ ከከተማዋ ወጥተው በሌላ አካባቢ የሚገኙ የሆስፒታሉ የሕክምና ባለሙያዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ያጋጠመው ችግር በከተማዋ እና በዙሪያዋ ያሉ ነዋሪዎች እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የሕክምና አገልግሎት እንዳያገኝ ያደርጋል።
Source: Link to the Post