ባለሥልጣናት በስማቸው የተመዘገበ የግል ድርጅትና የአክሲዮን ድርሻ እንዲያቋርጡ ወይም እንዲያስተላልፉ ሊገደዱ ነው፡፡የመንግሥት ባለሥልጣናት በግል ጥቅማቸውና በኃላፊነታቸው መካከል ለጥቅም ግጭ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/tyjYHFeqoW40MT1tiQviiHYl-ZHwea3LIaMuidd0IMQoPWhXHLKQeWRXpeF_WoEmxX7FyABVWbnkldx8C8N9ntuNvpgx-4eO2PcC7_zHzfYy0nPgsg1yiGLmNctc8ixWoVSD4LlX1y-XZyvgVqRrXOViv9hbyhI5KRfWm4cWNR2saklawByaDw1iiZNw2mpTlHRKGvlSiZxV_WSl0lxWS7919MV4ihP700t3uVPPmPdqFFFquockWlF6_CrwvCDl0A6dQFTuAoJidRqUtTce676stH_gAgKA9O8bdIV5zTP8xQOcX2IlFL27FboVNW3-2c9a5f0P7EI_Yw0Os2_hqQ.jpg

ባለሥልጣናት በስማቸው የተመዘገበ የግል ድርጅትና የአክሲዮን ድርሻ እንዲያቋርጡ ወይም እንዲያስተላልፉ ሊገደዱ ነው፡፡

የመንግሥት ባለሥልጣናት በግል ጥቅማቸውና በኃላፊነታቸው መካከል ለጥቅም ግጭት የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን መከላከልና ማስወገድ እንዲችሉ፣ በስማቸውና በቅርብ ቤተሰብ ባለቤትነት የተመዘገቡ የንግድ ኩባንያዎችን ወይም የአክሲዮን ድርሻዎችን፣ እንዲያቋርጡ አልያም እንዲያስተላፉ ሊገደዱ ነው፡፡

ይህንን ግዴታ በመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ለመጣል ያቀደው፣ በፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ መሆኑን የሪፖርተር ዘገባ ያመለክታል፡፡
ረቂቅ ደንቡ፣ ‹‹ማንኛውም የመንግሥት ባለሥልጣን በረቂቅ ደንቡ የተጠቀሱ ለጥቅም ግጭት የሚያጋልጡ ሁኔታዎችና መንስዔዎች መኖራቸውን ሲረዳ፣ የጥቅም ግጭቱን ማስወገድ አለበት›› የሚል ድንጋጌ ይዟል፡፡

በዚህም መሠረት ማንኛውም የመንግሥት ባለሥልጣን የጥቅም ግጭት የሚፈጥሩ፣ ወይም ግጭት ሊፈጥሩ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ ድርጊቶችን፣ አስቀድሞ ማወቅና ግጭቱን የማስወገድ ግዴታ ይኖርበታል፡፡

የጥቅም ግጭቱን ለማስወገድ ይገባቸዋል ተብለው ከተዘረዘሩት ተግባራት መካከልም፣ ‹‹ማንኛውም ባለሥልጣን ለጥቅም ግጭቱ መነሻ የሆነውን የግል ኢንተርፕራይዝ፣ ካምፓኒ ወይም የግል ድርጅት ድርሻውን ማስተላለፍ አልያም ማቋረጥ አለበት›› የሚለው ድንጋጌ ይገኝበታል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply