ባለስልጣኑ ሮም የገበታ ጨው ምርቶችን ከገበያ እየሰበሰበ መሆኑን ገለፀ፡፡

ሮም የገበታ ጨውንና ሴንሆን የማር ምርቶች ከገበያ እየሰበሰበ መሆኑን የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታዉቋል።

ሮም የገበታ ጨውና ሴንሆን የምርት ውጤቶች ተገቢውን የጤና ብቃት ማረጋገጫ ሳያወጡ ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ በመስራታቸውና የምርቶቹ ናሙና ተወስዶ በላብራቶሪ ሲመረመር መስፈርቱን ያላሟሉ በመሆናቸው ድርጅቶች ታሽገው ምርቶቹን በሁሉም ክ/ከተሞች ከገበያ እንዲሰበሰቡ እያደረገ መሆኑን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

የተሰበሰቡት ምርቶችም መመሪያውን በተከተለ መልኩ እንደሚወገዱም ተገልጿል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply