
በዚህ ባለንበት የዲጂታል ዘመን የሰው ልጆች በአካል ከሚያደርጉት መስተጋብር ይልቅ በማኅበራዊ ሚዲያ በኩል የሚያደርጉት እየበለጠ መጥቷል። ሁሉም ሰበር ዜና አድራሽ፣ ሁሉም አስተያየት ሰጪ ሆኗል። ደስታን እና ሐዘንን ለብዙኃኑ ማጋራት፣ በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ አስተያየት ያለገደብ መስጠት፣ በተፈጠሩ ኩነቶች ላይ የራስን አመለካከት ማንፀባረቅ ለሁሉም ሰው ቀላል ነው።
Source: Link to the Post