
ባለፈው ሳምንት ምግብና ነዳጅ ጭነው ወደ ትግራይ ተንቀሳቅሰው የነበሩ ከ20 በላይ ተሽከርካሪዎች በገጠማቸው ችግር ምክንያት መመለሳቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ ተናገሩ። ዶክተር ለገሠ ቱሉ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የትግራይ ኃይሎች በተቆጣጠሯቸው የአፋር ወረዳዎች በኩል የእርዳታ አቅርቦት ይዘው ወደ ትግራይ እንቅስቃሴ ጀምረው የነበረ ቢሆንም በህወሓት ኃይሎች ጉዟቸው መደናቀፉን ገልጸዋል።
Source: Link to the Post