You are currently viewing ባለፈው ዓመት በብአዴን የጸጥታ አካላት በግፍ የተገደሉ ጀግና የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አባለት ተዘከሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    መጋቢት 3 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ…

ባለፈው ዓመት በብአዴን የጸጥታ አካላት በግፍ የተገደሉ ጀግና የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አባለት ተዘከሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 3 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ…

ባለፈው ዓመት በብአዴን የጸጥታ አካላት በግፍ የተገደሉ ጀግና የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አባለት ተዘከሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 3 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ባለፈው ዓመት ብአዴን ባሰማራቸው የጸጥታ አካላት በጥይት በግፍ የተገደሉ ጀግና የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አባለት ዛሬ መጋቢት 3/2015 ተዘከረዋል። በምዕራብ እና ምስረቅ ጎጃም አካባቢ የህዝባዊ ኃይሉ ደጀን እና አመራር በመሆን የአማራን ህዝብ መብት፣ ጥቅም እና ፍላጎትን ለማስከበር ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩት:_ 1) ፋኖ እናውጋው ታደለ፣ 2) ፋኖ አዲሱ ቢተው፣ 3) ፋኖ አጃናው አዲሱ፣ 4) ፋኖ ፀሀይ አለምነህ፣ 5) ፋኖ አናጋው በላይ እና 6) ፋኖ መዝገብ ሞላልኝ መጋቢት 3/2015 በዳንግላ ከተማ በህዝባዊ ኃይሉ አባላት እና በቤተሰቦቻቸው ተዘክረዋል። የተሰው ፋኖዎች ቤተሰቦቻቸው እና ጓዶቻቸው የሰማዐታቱ ህልም የነበረውን የአማራ ህዝብን ጥቅም የማስከበር እና ኢትዮጵያን አፅንቶ የማቆየት ህልም ከምንጊዜው በላቀ መልኩ ለማስቀጠል የበለጠ እንደሚሰሩ በአንደኛ ዓመት ዝክረ በዓሉ ላይ በቁጭት በመግለጽ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥሪ ስለመቅረቡ የጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ዘገባ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply