You are currently viewing ባለፉት ሰባት ወራት ወደ ውጪ ከተላኩ የጨርቃጨርቅ ውጤቶች ከ87 ሚሊየን ዶላር በላይ ተገኘ

ባለፉት ሰባት ወራት ወደ ውጪ ከተላኩ የጨርቃጨርቅ ውጤቶች ከ87 ሚሊየን ዶላር በላይ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ባለፉት ሰባት ወራት ወደተለያዩ አገሮች ከተላኩ የጨርቃጨርቅ ስፌት ኢንዱስትሪ ዘርፍ ምርቶች ከ87 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ መገኘቱን የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
ኢንስቲትዩቱ ይህን ያስታወቀው የሰባት ወር ዕቅድ አፈጻጸሙን በቢሾፍቱ ከተማ በገመገመበት ወቅት ነው።
የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ለማ ÷ኮቪድ-19 በጨርቃ ጨርቅ ዘርፉ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አሳርፎ ቆይቷል ብለዋል።
በአገር ውስጥ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የኮቪድ-19 ተጽእኖን ተቋቁመው ምርታቸውን እንዲያሳድጉ በተሰራው ስራ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን አስረድተዋል።
በዚህም ባለፉት ሰባት ወራት በአገሪቱ የሚገኙ የጨርቃጨርቅ ስፌት ኢንዱስትሪዎች ወደ ውጪ ከላኩት የጨርቃጨርቅ ስፌት ዘርፍ ምርት ከ87 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ መገኘቱን ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ የግል ባለሃብቶችን በመደገፍ ሰራተኞቻቸው በክህሎትና በእውቀት እንዲበቁ ከማድረግ አንጻርም የተለያዩ ተግባራት ማከናወኑን ጠቅሰዋል።
ባለፉት ሰባት ወራትም ከስምንት ሺህ በላይ ለሆኑ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠቱን ተናግረዋል።
በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታትም የጥናትና ምርምር ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
በስራ ዕድል ፈጠራ በሰባት ወራቱ ለ5 ሺህ 647 ዜጎች የስራ ዕድል እንዲፈጠር ማድረጉም ተጠቅሷል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Comment
Share

The post ባለፉት ሰባት ወራት ወደ ውጪ ከተላኩ የጨርቃጨርቅ ውጤቶች ከ87 ሚሊየን ዶላር በላይ ተገኘ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply