ባለፉት ስድስት ወራት በኢትዮጵያ ከ440 ሺ በላይ ሰዎች የጸረ ኤች አይ ቪ ኤድስ መድኃኒት እንደወሰዱ ተነገረ፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ3 ነጥብ 2 ሚሊየን የህብረተሰብ ክፍሎች የኤች.አይ.ቪ ምክር እና ምርመራ ማድረግ እንደተቻለ የተናገረው የጤና ሚኒስቴር ከአምናው አንጻር ምርመራውን ያገኘው የህብረተሰብ ክፍል እንደቀነሰ ገልጿል፡፡

ቀደም ብሎ በዘመቻ መልኩ ሲሰጥ የነበረው የቅስቀሳ ስራ መቅረቱ ለምርመራው መቀነስ ምክንያት መሆኑን በጤና ሚኒስቴር የፖሊሲ ፕላን ቁጥጥር እና ግምገማ አማካሪው አቶ ጸደቀ ማቲዮስ ተናግረዋል፡፡የምርመራ ቁጥሩ ቢቀንስም የተያዙ ሰዎች ቁጥር ግን መጨመር ማሳየቱን አያይዘው ገልጸዋል፡፡

የበሽታው ስርጭት አሁንም በጋምቤላ እና በአዲስ አበባ መጨመር ማሳየቱን የጠቀሱት አቶ ጸደቀ ሪፖርቱ የትግራይ ክልልን ያላካተተ እንደመሆኑ በቀጣይ ያለውን የስርጭት መጠን የማወቅ እና መወሰድ የሚገባቸው ስራዎች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ቀን 19/06/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply