ባለፉት ሶስት አመታት በስፖርታዊ ውድድሮች ላይ የተከለከሉ መድሀኒቶች ተጠቅመው የተገኙ 16 አትሌቶች መታገዳቸው ተገለጸ፡፡

ከተቋቋመ ሶስት አመታት ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጸረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት እስካሁን ድረስ የተቀመጡትን ህጎች ተላልፈው የተገኙ አትሌቶች ከውድድር ማገዱን አስታውቋል፡፡

የጽፈት ቤቱ ዋና ዳሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ከውድድር የታገዱት አትሌቶች ከአራት አመት አንስቶ እስከ አስራ ስድስት አመት በየትኛውም ውድድር እንዳይሳተፉ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በውድድር እንዳይሳተፉ እግድ የተጣለባቸው አትሌቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ተፈጻሚ የሚሆን ነውም ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የተከለከሉ ንጥረ ነገሮችንና ሌሎች ተዛማጅ ቅመሞችን ከቦታ ቦታ ማዘዋወር ከአራት ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ የሚያስቀጣ ሲሆን አትሌቶች የተከለከሉ ንጥረ ነገሮችንና መድኃኒቶችን እንዲጠቀሙ ማገዝ በተመሳሳይ ከአራት ዓመት ጀምሮ እስከ ዕድሜ ልክ ቅጣት እንደሚያስቀጣ ጽፈት ቤቱ ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅህፈት ቤት በቀጣይም የምርመራና ቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply