ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተቀጠሩ 14 ሺህ ሰራተኞች ውስጥ 76 በመቶዎቹ መልቀቃቸው ተገለጸ።በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢ…

ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተቀጠሩ 14 ሺህ ሰራተኞች ውስጥ 76 በመቶዎቹ መልቀቃቸው ተገለጸ።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢንዱስተሪ ፓርኮችን የስራ አፈጻጸም በመገምገም ላይ ይገኛል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከተፈጠረው 14 ሺህ 665 የስራ ዕድል ውስጥ 11 ሺህ 169 ዎቹ ስራ መለቀቃቸው ተነግሯል።

ይህም የሰራተኞችን የስራ መልቀቅ ምጣኔ 76 በመቶ አድርሶታል ተብሏል።

ቋሚ ኮሚቴው በየጊዜው የሰራተኞች የስራ መልቀቅ እየጨመረ መጥቷል የፍልሰቱ ምክንያት ምንድን ነው ሲል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን ጠይቋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ወይዘሪት ሌሊሴ ነሜ ለቋሚ ኮሚቴው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ኮሚሽነሯ እንዳሉት ለሰራተኞች ፍልሰት ዋና ዋና ምክንያቶች በፓርኮች የመኖሪያ ቤት አለመኖር እና ትራንስፖርት እጥረት ነው ብለዋል።

ሰራተኞች ከ100 ኪሎ ሜትር በላይ ራዲየስ ርቀት ላይ የሚመጡ በመሆኑ እና የተደረገው የደመወዝ ማስተካከያው አርኪ በአለመሆኑ ፍልሰቱን አባብሶታል ብለዋል ኮሚሽነሯ።

80 በመቶ የሚሆነውን የሰራተኞች ፍልሰት ምክንያት የመኖሪያ ቤት ችግር ነው ፤ ይህንን ለመቅረፍ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የመኖሪያ ቤት ግንባታ የጀመሩ ባለሀብቶች አሉ እሱን በሁሉም ፓርኮች የማስፋፋት ስራ ያስፈልጋልም ብለዋል።

ዳንኤል መላኩ
ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply