ባለፉት አምስት ዓመታት በአማሮ እና በጉጂ ዞን አዋሳኝ ቦታዎች የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት ሸንጎ ተሰየመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ…

ባለፉት አምስት ዓመታት በአማሮ እና በጉጂ ዞን አዋሳኝ ቦታዎች የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት ሸንጎ ተሰየመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ላለፉት አምስት ዓመታት በደቡብ ክልል በአማሮ ልዩ ወረዳ እና በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ተፈጥሮ የተነበረዉን ግጭቶች ለመፍታት የእርቅ ስነስርዓት እየተካሄደ ይገኛል ተባለ። ከሐምሌ 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ተነስተዋል የተባሉ ታጣቂ ቡድኖች አዋሳኝ በሆነችዉ በአማሮ ልዩ ወረዳ በሚገኙ አጎራባች ቀበሌዎች ላይ በተደጋጋሚ በከፈቱት ጥቃት ለበርካታ ዜጎች ሞት፣ ለአካል ጉዳት እና ለንብረት ዉድመት እንዲሁም ከመኖሪያ ቤት መፈናቀል ምክንያት መሆኑ ተነግሯል። ባለፉት አምስት ዓመታት በልዩ ወረዳዉ ተፈጥሮ በነበረዉ ግጭት እንዲሁም በሶስት ወቅቶች በተለያዩ ምክንያቶች ተከስቶ በነበረዉ ድርቅ ከ 140 ሺህ 600 በላይ ዜጎች ተጎጂ መሆናቸዉ ይታወቃል። ህዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም. እየተካሄደ በሚገኘዉ የእርቅ ስነስርዓት ከሁለቱም ወገኖች የተወጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎችም ተሳታፊዎች መሆናቸዉ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል። “የግል ፍላጎታቸዉን ለማሳካት በማሰብ የሁለቱ ህዝቦች መልካም ግንኙነት ለማደፍረስ እንዲሁም የአካባቢውን ሰላም ሲያውኩ የቆዩ መኖራቸዉ” እየተካሄደ በሚገኘዉ ስነስርዓት ተገልጿል። ለግጭቱ መነሻ ምክንያት የነበረዉ ለአማሮ ልዩ ወረዳ አጎራባች የሆነዉ የጉጂ ኦሮሚያ ነዋሪዎች በሚያነሱት “የወሰን ይገባኛል” ጥያቄ በተደጋጋሚ እየወሰዱት የሚገኘዉ የድንበር ማስፋፋት እርምጃ እንደሆነ ከአሁን ቀደም የዘገቡን በማስታዎስ ያጋራው አዲስ ዘይቤ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply