You are currently viewing “ባለፉት ዓመታት በተለይ በ2012 ዓ.ም ከክልሉ ውጭ የሚገኙ የአማራ ተማሪዎች ላይ በተደጋጋሚ በሚደርስ ብሔር ተኮር ጥቃት ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ሕይወታቸው አልፏል፣ ከታገ…

“ባለፉት ዓመታት በተለይ በ2012 ዓ.ም ከክልሉ ውጭ የሚገኙ የአማራ ተማሪዎች ላይ በተደጋጋሚ በሚደርስ ብሔር ተኮር ጥቃት ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ሕይወታቸው አልፏል፣ ከታገ…

“ባለፉት ዓመታት በተለይ በ2012 ዓ.ም ከክልሉ ውጭ የሚገኙ የአማራ ተማሪዎች ላይ በተደጋጋሚ በሚደርስ ብሔር ተኮር ጥቃት ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ሕይወታቸው አልፏል፣ ከታገቱትንና እስካሁንም አድራሻቸው ካልታወቀው 17ቱ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተጨማሪ ….” ‹‹ዘመቻ ምኒልክ ቁ-3››ን አስመልክቶ ከአማራ ተማሪዎች ማህበር(አተማ) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የአማራ ሚዲያ ማእከል… መስከረም 21 2015 አ/ም አዲስ አበባ የአማራ ተማሪዎችን ሁለንተናዊ ደኅንነት ማስጠበቅ፣መብታቸውንና ጥቅማቸውን ማስከበር፣ ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎችን ማፍራት እና እንደ ሕዝብ ደግሞ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ያገኙ ዘንድ ሰላማዊ ትግል ማድረግ ከማህበሩ መሠረታዊ ዓላማዎች መካከል ናቸው፡፡ማህበሩ ባለፉት ሦስት ዓመታት በተማሪዎች እና ሌሎች በጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ ባለፉት ዓመታት በተለይ በ2012 ዓ.ም ከክልሉ ውጭ የሚገኙ የአማራ ተማሪዎች ላይ በተደጋጋሚ በሚደርስ ብሔር ተኮር ጥቃት ምክንያት በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ሕይወታቸው አልፏል፣ ከታገቱትንና እስካሁንም አድራሻቸው ካልታወቀው 17ቱ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተጨማሪ ብዙዎች ትምህርታቸውን ባቋረጡበትና ወደ ቤታቸው በተመለሱበት ጊዜ ወደ ትምህርታቸው ይመለሱ ዘንድ ባደረገው ጥረት ምንም እንኳን ለደኅንነታቸው አስተማማኝ ዋስትና ባልነበረበት ሁኔታ ቢሆንም በቀጣዩ ዓመት እንዲመለሱ ለማድረግ ተችሏል፡፡ እንደሚታወቀው ከሕወሃት ቡድን ጋር በሚደረገው ጦርነት በአማራ ሕዝብ ላይ በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ደርሷል፤ እየደረሰም ይገኛል፡፡ ይህ ጦርነት ሕጻናትን ያለአሳዳጊ አስቀርቷል፣ አረጋዊያንን ያለጧሪ አስቀርቷል፣ በርካታ ቤተሰቦችን ያለሰብሳቢ አስቀርቷል፣ የሕዝብ መገልገያ ተቋማትና የግለሰብ ንብረቶች ወድመዋል፣ ያሳደረው የሥነ ልቦና ቀውስም በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ይህን ተከትሎ ማህበሩ በዋናነት ሁለት ፕሮክቶችን በመቅረጽ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ የመጀመሪያው በጦርነቱ የተሠዉ ሚሊሻዎች እና ፋኖዎች ቤተሰቦችን መደገፍ ሲሆን ማህበሩ ከ‹‹አማራ ኢመርጀንሲ ፈንድ(AEF)›› በተገኘ ከ12 ሚሊዬን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ከ3500 በላይ ለሚሆኑ በጦርነቱ የተሠዉ ሚሊሻዎችና ፋኖዎች ቤተሰቦች ለእያንዳቸው የ4000 ብር የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በጦርነቱ ምክንያት ወላጆቻቸውን ያጡ ከ350 በላይ ሕጻናትን ጥናት አድርጎ በመለየት በቋሚነት የሚደገፉበት ፕሮጀክት ሲሆን የአማራ ኢመርጀንሲ ፈንድ አጋር ድርጅት ከሆነው ‹‹ወንፈል ተራድኦ ድርጅት›› ጋር በመተባበር ለቀጣዮቹ 18 ዓመታት በቋሚነት ድጋፍ እንዲያገኙና ትምህርታቸውን እንዲማሩ ማድረግ ተችሏል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት ተግባራት በተጨማሪ ባሳለፍነው ዓመት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በተፈተኑ ተማሪዎች ላይ የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ በወቅቱ ችግሩ እንዲስተካከል ሰላማዊ ትግል ከማድረግ በተጨማሪ በድጋሚ እንዲፈተኑ መወሰኑን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም፤ ከ‹‹አማራ ሙያተኞች ህብረት በአሜሪካ›› ጋር በመተባበር በጦርነቱ ቀጥተኛ ተጎጂ በነበሩ 6 ዞኖች(ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ፣ሰሜን ጎንደር፣ደቡብ ጎንደር፣ሰሜን ወሎ፣ደቡብ ወሎ እና ዋግኽምራ፡- ሰሜን ሸዋ ዞን በራሱ አቅም ትምህርቱ እንዲሰጥ ማድረጉን ልብ ይሏል) የሚገኙ ተማሪዎችን ከክልሉ ትምህርት ቢሮና በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት ተቋማት ጋር በመነጋገር እና ለመምህራን ደመወዝ በመክፈል የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሰጥ አድርጓል፡፡ ማህበሩ ምንም እንኳን ባለበት የሀብት ውስንነት ምክንያት በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ትምህርቱ እንዲሰጥ ማድረግ ባይችልም የደረሰባቸውን ሁለንተናዊ ጉዳት እና በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ታሪካዊ ትስስር፣ትብብር እና ወንድማማችነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ አፋር ሂዶ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በመወያየትና ከ230 በላይ ለሚሆኑ የዩኒቨርሲቲ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራን መጠነኛ ደመወዝ በመክፈል ባለፈው ዓመት ተፈትነው ወደ ዩኒቨርሲቲ ሳይገቡ የቀሩና በዚህ ዓመት የሚፈተኑትን ጭምሮ በድምሩ ከ6500 በላይ የሚሆኑ የአፋር ክልል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲወስዱ አድርጓል፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ተግባራት ስኬታማ እንዲሆኑ በሐሳብ፣በጉልበት እና በገንዘብ ድጋፍ ስታደርጉልን ለነበራችሁ ከውጭ የአማራ ኢመርጀንሲ ፈንድ(AEF)፣ ወንፈል ተራድኦ ድርጅት፣የአማራ ሙያተኞች ህብረት በአሜሪካ(APU)፣ የአማራ ማህበር በአሜሪካ(AAA)፣የአማራ ማህበር በኮሎራዶ፣የአማራ ሕዝብ ሲቪክ ማህበራት በዩናይትድ ኪንግደም፣፣የአማራ ማህበር በኒው ኢንግላንድ እና ሌሎች ስማችሁ ያልተጠቀሰ በአማራ ስም የተደራጃችሁ የውጭ ማህበራትና ድርጅቶች ከሀገር ውስጥ ደግሞ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ፣የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ፣በየደረጃው ያላችሁ የትምህርት ተቋማት፣የአማራ ምሁራን መማክርት፣ የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም እና በውጭም በሀገር ውስጥም ሆናችሁ ልዩ ድጋፍ ላደረጋችሁ ግለሰቦች ሁሉ እሰካሁን ላደረጋችሁልንና በቀጣይም በሁሉም ዘርፍ በሚደረገው ትግልና ርብርብ ለምታደርጉት ያልተቆጠበ ድጋፍና አጋርነት ሁሉ በአማራ ተማሪዎች እና በመልካምነታችሁ በተጠቀሙ ወገኖች ሁሉ ስም ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ከዚህ ባሻገር ማህበሩ ባለፉት ሁለት ዓመታት፤ በርካታ በሀገር ውስጥ የሚገኙ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ድርጅቶች፣ ግለሰቦች፣ በውጭ የሚገኙ ማህበራትና ድርጅቶች፣ ግለሰቦች የተሳተፉበት፤ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎችና ትምህርት ቤቶች(ቤተ መጻሕፍት) የሚውል ‹‹ዘመቻ ምኒልክ›› የተሰኘ የትምህርት ቁሳቁስ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በዚህ ዓመትም ‹‹ዘመቻ ምኒልክ ቁ-3››ን ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ከዘመቻው መሠረታዊ ዓላማዎች መካከል የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ባለመቻላቸው ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎችን መደገፍ፤በተለይም ደግሞ በሁሉም አቅጣጫ ከቀያቸው በግፍ ተፈናቅለው በየመጠለያ ካምፑ የሚገኙና ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ማስቻል፣ የትምህርት መርጃ መጻሕፍት እጥረት ያለባቸውን ቤተ መጻሕፍት በመለየት የሚቻለውን ያክል ጉድለቶቹን መሙላት እና ማህበሩ ወልቃይት ላይ ሊያስገነባ ላሰበው የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት (ማንነቱን፣ባህሉን እና ታሪኩን ተነጥቆ የቆየውን የወልቃይት አማራ ሕዝብ በማንበብ እውነተኛ ታሪኩን፣ባህሉንና ማንነቱን እንዲያጤን ለማስቻል) መጽሐፍትንና አስፈላጊ የዲጅታል መርጃ መሣሪያዎችን ማሟላት በዋኛነት ይጠቀሳሉ፡፡ ዘመቻው ከመስከረም 21/2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 01/2015 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ይህንን ለማስፈጸም በየአካባቢው ጊዜያዊ ግብረ ሃይል ተቋቁሟል፡፡ በዘመቻው ወቅት የሚሰበሰቡ ቁሳቁሶች ኮምፒውተር፣ መጽሐፍት(የትምህርት መርጃ፣የታሪክ፣ የስነ ልቦና….ወዘተ)፣ደብተር፣እስክርቢቶ እና የመሳሰሉት ሲሆኑ በጥሬ ገንዘብ መርዳት የምትፈልጉ ማህበሩ ባዘጋጃቸው የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች ገቢ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ዘመቻው በዋናነት ከታች በተጠቀሱት ከተሞችና ዞኖች የሚካሄድ ይሆናል፡- ማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ደቡብ ጎንደር ዞን፣ባሕር ዳር ከተማ፣ ምዕ/ጎጃም ዞን፣ምስ/ጎጃም፣አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ሰሜን ሸዋ ዞን እና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲሆኑ ሌሎች ዞኖች አሁን ከሚገኙበት ወቅታዊ ሁኔታና በጦርነቱ ከደረሰባቸው ቀላል የማይባል ጉዳት አንጻር ተጨማሪ ጫና እንዳይፈጥር በመስጋት ዘመቻው የማይካሄድባቸው ናቸው፡፡ ሆኖም ግን በእነዚህ አካባቢዎች መርዳት የምትፈልጉና ሌሎች በጥሬ ገንዘብ መርዳት የምትፈልጉ በማህበሩ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች፡- የአትዮጵያ ንግድ ባንክ፡-1000461162634 አባይ ባንክ፡-2011117843731018 አቢሲንያ ባንክ፡-90028014 ዳሸን ባንክ፡-5020813382011 አቢሲንያ ባንክ፡-73926227 በመጠቀም ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ድጋፍ ለማድረግ ከዚህ በታች የተገለጹትን አድራሻዎች መጠቀም የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡- ባሕር ዳር ስ.ቁ፡-0915857345 አድራሻ፡- ቀበሌ 04 ‹‹መሥራት ያስከብራል›› ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 191 ደብረ ብርሃን(ሰሜን ሸዋ) ስ.ቁ፡-0981344385 አድራሻ፡-ጠባሴ ቡና ባንክ የሚገኝበት ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 ጎንደር(ማዕከላዊ ጎንደር) ስ.ቁ፡-0937378182 አድራሻ፡- ፒያሳ ‹‹መድኃኔዓለም›› ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ደብረ ታቦር ስ.ቁ፡-0933573700 አድራሻ፡-ቴዎድሮስ አደባባይ ከሚገኘው የአብን ቢሮ ጎን ካለው ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ፍኖተ ሰላም ስ.ቁ፡-0901412023 ደብረ ማርቆስ ስ.ቁ፡-0932797078 አዲስ አበባ ስ.ቁ፡-0977726680 አድራሻ፡- 4 ኪሎ አልማ ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ‹‹የተባበሩት አማራ በጎ አድራጎት ማህበር›› ቢሮ ሲሆን በማህበሩ ስልኮች በ09 18 38 88 38 ወይም በ058 847 06 28 መጠቀም የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በመሆኑም በውጭ የምትገኙ በአማራ ስም የተዳራጃችሁ ማህበራትና ድርጅቶች፣በሀገር ውስጥ የምትገኙ የመንግሥት ተቋማት(ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ)፣ መንግሥታዊ ያልሆናችሁ የልማትና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ባለሃብቶች፣የንግድ ተቋማት(ባንኮችን ጨምሮ) እና ነጋዴዎች፣ መምህራን፣ በጎ አድራጊ ግለሰቦች በአጠቃላይ መላው ሕዝብ በዚህ ትውልድ የመቅረጽና የማስቀጠል ታሪካዊ ዘመቻ አሻራችሁን ታሳርፉ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ አተማ፡የአማራ ትውልድ ተቋም!!! መስከረም ፳/፳፻፲፭ ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply