
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 27፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 3 ሺህ 934 የላቦራቶሪ ምርመራ 281 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
ዶክተር ሊያ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት 203 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡
እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት 13 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
እስካሁን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች 112 ሺህ 813 ሲደርስ 1 ሺህ 963 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው 11 ሺህ 463 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 245 ሰዎች ደግሞ በጽኑ የታመሙ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡
ወረርሽኙ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 826 ሺህ 56 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡
ከእነዚህም መካከልም 126 ሺህ 241 በወረርሽኙ የተያዙ ሲሆን አሁን ላይ 11 ሺህ 463 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
The post ባለፉት 24 ሰዓታት 322 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 203 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.
Source: Link to the Post