ባለፉት 24 ሰዓታት 397 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 701 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 242 የላብራቶሪ ምርመራ 397 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።

እንዲሁም 701 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

ይህም ወረርሽኙ ከገባ ጀምሮ እስካሁን 103 ሺህ 681 ሰው ከቫይረሱ ማገገሙን መረጃው ያመላክታል፡፡

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት የ8 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 861 ደርሷል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 747 ሺህ 905 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 120 ሺህ 348 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 14 ሺህ 804 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 265 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም መረጃው ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

 

The post ባለፉት 24 ሰዓታት 397 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 701 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply