ባለፉት 8ወራት 220ሺ ዩኒት ደም ተሰብስቧል ተባለ።በ2016 በጀት አመት ባለፉት 8 ወራት ውስጥ 320ሺ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ 220ሺ ዩኒት ደም መሰብሰብ መቻሉን የኢትዩጵያ ደምና ህ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/o7-ZftiHF3hZWMzbaq5TXF1TSjVAvLyTO3tAnGzkx5F94eHi_A4gsGTI8p_FVX5UWCE6Odr5e_kLwm25dzaRh88B1VCdVp2LKVqHuS02Mv-9Juuu8yRQ_ziB4J0XQunJKH8eRlsms5XkWXAvhF56KGN-nnHpPB6OtJnKzUXqFItT982VLolmKOAUFWhfYCEU3OrxBLX9-lrjeio-oVaCn7R0MDnuCY8HWu0vQAlVEJbeP6TQznj0x5aIqzhSZjHWlmQYWLK9x1oqKLopCEZ7jvy7IMdZL4UVrJAA4PH7i4xDkJMbB2Ao5SlQbZrEutFYJJwQgIqlAeVS2sQZ0hf07g.jpg

ባለፉት 8ወራት 220ሺ ዩኒት ደም ተሰብስቧል ተባለ።

በ2016 በጀት አመት ባለፉት 8 ወራት ውስጥ 320ሺ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ 220ሺ ዩኒት ደም መሰብሰብ መቻሉን የኢትዩጵያ ደምና ህብረ ህዋስ አገልግሎት አስታውቋል።

አዲስ አበባ ብቻ 80 ሺ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ የታቀደ ቢሆንም መሰብሰብ የተቻለው ግን ከዛ በታች መሆኑን ነው የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ተናግረዋል፡፡

አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ በቀን ከ350 እስከ 400ዩኒት ደም የህክምና ፍላጎቱን ለማሟላት ያስፈልጋል ያሉት ዳይሬክተሩ በዚህ ሳምንት ውስጥ ብቻ በቀን ከ250 እስከ 300 ዩኒት ደም መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።

ይሁን እንጂ አሁንም የደም ፍላጎቱን ለማሟላት በቂ አይደለም ሲሉም አክለዋል።

አሁን ደግሞ ወቅቱ የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮች የፆም ወቅት በመሆኑ በቂ ደም እንደማይኖር ገልፀዋል።

ህብረተሰቡ ደም እንዲለግስ ጥሪ ያቀረቡት አቶ ሀብታሙ ይህ የያዝነው መጋቢት ወር ደም የመለገስ ወር እንዲሆን የተደረገ ሲሆን ሁሉም ህብረተሰብ ደም እንዲለግስ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply