ባለፉት 9 ወራት 837 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን እንዳጡ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቋል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መሳፍንት እሸቴ ለአሐዱ እንዳሉት በተያዘው በጀት አመት ባለፉት 9 ወራት ከ3 ሺህ 600 መቶ በላይ አሽከርካሪዎች ላይ ደንብ በመተላለፋቸው ምክንያት ክስ ተመስርቷል፡፡

አክለውም በነዚህም ወራት ውስጥ 1ሺህ 768 አደጋዎች የደረሱ ሲሆን 8 መቶ 37  ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ 1 ሺህ 588 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ኢንስፔክተር መሳፍንት ገልፀዋል፡፡

ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ36 ሰዎች ሞት ጭማሬ ያሳየ ሲሆን የ22 ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ለውጥ መመዝገቡን ዋና ኢንስፔክተሩ ጠቁመዋል፡፡በተጨማሪ ከ49 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የወጣባቸው ከ577 በላይ ተሸከርካሪዎች መውደማቸውን ተናግረዋል፡፡

ቀን 10/09/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post ባለፉት 9 ወራት 837 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን እንዳጡ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቋል፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply