ባለፊት አምስት አመታት ለእሳትና ለድንገተኛ አደጋዎች በተሰጠው ፈጣን ምላሽ ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ ከውድመት ማዳን መቻሉ ተገለጸ። በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አምስት አመታት የእሳትና ሌሎ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/olmX2n-RtJyY35TOh11o2y918YJa3v1HzYRSBB4gWEbQb7_9NXAgri_8w1QBEClyWgCD8IeclPjUBFUW6m8JfXyKV8jNvVn57FWpt7SaZsTkQLZee67-Iu9qzlAbJOiE8RM9-N9KGVaSGL8DcuIuSoip-WUiQQi-xTzlC2z3QPZTdOeAphAii5EgWw7ilXSGsGGDIduUN9-s78p3mYzi_3O6MTMvEiqiA6fiQpcPNmkAtT5FACHf9DxrrOExD5UxZl4v344PgdfmIdm2sIM2Xj33HeHTJP33_Fx31wo3eZzxDbBRl-Q5QK7fRINmGJfthY7DAidZBF4OFUtHySLHWA.jpg

ባለፊት አምስት አመታት ለእሳትና ለድንገተኛ አደጋዎች በተሰጠው ፈጣን ምላሽ ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ ከውድመት ማዳን መቻሉ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አምስት አመታት የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎችን ለመቆጣጠር በአደጋ ምላሽ ዘርፉ በተሰጠ ፈጣን ምላሽ 70 ቢሊዮን 101 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ከዉድመት ማዳን መቻሉ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ባለፉት አምስት አመታት በደረሱት አደጋዎች ምክንያት ህይወታቸዉ አደጋ ዉስጥ የነበሩ 165 ሰዎችንም መታደግ ተችሏል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት ተቋሙ አስፈላጊው ግብአትና በቴክኖሎጅ በማጠናከር የአደጋ መከላከልና መቆጣጠር አቅሙን እያሳደገ ይገኛል ብለዋል።

በመዲናው የሚከሰቱ የእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎችን በፍጥነት በመቆጣጠር ከተማዋ ደህንነቷ የተጠበቀ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ ንጋቱ ማሞ ለጣበያችን ተናግረዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply