ባለፍት ሶስት ዓመታት በኦሮሚያና አፋር ክልሎች 1 መቶ ሹፌሮች ተገለዋል ተባለ፡፡ የጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ባለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ 1መቶ የሚደርሱ የከባድ መኪና አሽከር…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/MRkIuk_IH7KXQwPyEUGgOpKrkVdPRbR7it2Dw7YZhHauso8n0JFUs8Mcziha_pvKb8-tbn2OzfI3SRIeZvNJCkVB1-iaNwmBkvqNq5YhImBRlgdysagbnwO2q7xZVDYsOaL5Fb1huMF50Ujah2SICJKrDWMwoOcn7KsbSiZKnAFSgyCZFwj5MVC4Jh1m6zD5XkN9jJicOnVoiNRWajtwpcOErN-K21vBW-kbPvq3Qkzgqg1rRuNwTOi9BtsJtP26yDgsjpkZyw8pZgHZwhBO3OPiIhbHg391f5EhXCyPLvva1PdL2M-yWUSV6UnTW4MVsY6P8LvclD22U4q2Qo1Bhw.jpg

ባለፍት ሶስት ዓመታት በኦሮሚያና አፋር ክልሎች 1 መቶ ሹፌሮች ተገለዋል ተባለ፡፡

የጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ባለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ
1መቶ የሚደርሱ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ለጣቢያችን ተናግሯል።

የማህበሩ ፀሀፊ አቶ ሰጡ ብርሀን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በሹፊሮች ላይ የሚደረገው እንግልት እንደበዛ በማንሳት 1 መቶ የሚደርሱ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች መገደላቸውን ጠቁመዋል።

የአሽከርካሪዎች እገታ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ማስከፍል፣ ድብደባ፣ ግድያ እና የንብረት ውድመትም ልላው ጉዳይ እንደሆነ አቶ ሰጡ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም እነዚህ ድርጊቶች በ ኦሮሚያ፣ አፋር እንዲሁም ሌሎች ክልሎች ተባብሰው የቀጠሉ በመሆኑ ሁኔታው አሳሳቢ እንደሆነም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘውዱ ከዚህ ቀደም ለጣቢያችን እንደገለፁት አሽከርካሪዎች ላይ እገታና የንብረት ውድመትን ጭምሮ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱባቸው እንደሆነም ገልፀዋል።

አቶ ሰለሞን ለፌድራለ ፖሊሰ ለመከላከያ እንድሁም ለኦሮሚ ክልል ፖሊሰ ችግሮቹን ለይተው ጥያቄ ቢያቀርቡም የሚሰጠው ምላሽ እንዲሁም የሚወሰድው አርምጃ ችግሩን በዘላቂነት እንዳልቀረፈም መናገራቸው ይታወሳል።

በለአለም አሰፋ

መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply