
ባለ ሶስት እና ባለ አራት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ እንዳያሽከረክሩ ታገዱ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥን በተሻለ መልክ ለመምራት የሚያስችል የአሰራር ማሻሻያ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም የአሰራር ማሻሻያ ስራው ተጠናቆ እንዲሁም የአገልግሎቱ አስፈላጊነት በዝርዝር ተጠንቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ከነገ የካቲት 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ በየትኛውም አከባቢ ላልተወሰነ ጊዜ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት የታገደ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል፡፡
የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም
Source: Link to the Post