You are currently viewing ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በእለተ እሁድ ግንቦት 13/2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)    ግ…

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በእለተ እሁድ ግንቦት 13/2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግ…

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በእለተ እሁድ ግንቦት 13/2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 12/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ እሁድ ግንቦት 13/2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ ዝግጅቴን አጠናቅቄ ጉባያተኞቹንና የክብር እንግዶቹን ለመቀበል በመጠባበቅ ላይ እገኛለሁ ያለው ባልደራስ ከአሁን ቀደም ጉባኤውን እንዳያካሂድ በተደጋጋሚ ስርዓታዊ ክልከላ እና የአመራሮች እንዲሁም የአባላት እስር የገጠመው ፓርቲ መሆኑ ይታወቃል። ባልደራስ እያጋጠመው ያለውን ተደጋጋሚ ክልከላ እና መስተጓጎልን ለማስቀረት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ስብሰባው ከሚደረግበት ሆቴል ጋር ውል የመግባት እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማሳወቅ ስራ ማከናወኑ ተገልጧል። ሁሉም የሚዲያ ተቋማት በስፍራው ተገኝተው የዘገባ ሽፋን እንዲሰጡም ጥሪ አድርጓል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply