ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አላግባብ ለወራት ታስረውብኛል ያላቸው አመራሮቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 1 ቀ…

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አላግባብ ለወራት ታስረውብኛል ያላቸው አመራሮቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጠየቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሚክራሲ ፓርቲ የባልደራስ ፕሬዝዳንትን አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አላግባብ በቀጣዩ ምርጫ እንዳይሳተፉ ለማድረግ ሲባል በፈጠራ ክስ ከታሰሩብኝ ወራትን አስቆጥረዋል ያላቸው አመራሮች እንዲፈቱለት ጠይቋል። የባልደራስ አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር/ቀለብ ስዩምና አስካለ ደምሌ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ የሚጠይቀውና ለአንድ ወር ይቀጥላል የተባለው የፍትህ መጠየቅ አለም አቀፍ ዘመቻ ዛሬ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም መግለጫ በመስጠት ተጀምሯል። በመግለጫው “ለውጥ መጣ” ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የተከሰቱ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ምስቅልቅሎችን የዳሰሰ መሆኑን ተመልክተናል። በተለይ የፍትህ ሂደቱ ላይ የተደቀኑ ፈተናዎች ዛሬም ከትናንቱ አካሄድ ፈቀቅ ለማለት የተቸገርን መሆናችንን መግለጫው አሳይቷል። ይህ ለጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ ለአለም አቀፍ ተቋማትና ለሌሎች ባለስልጣናትም ግልፅ ደብዳቤ መጻፍን፣ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን፣የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ማካሄድንና የመሳሰሉት ተግባራት የሚከናወኑበት ዘመቻ በባልደራስ ዋና ጽ/ቤት ለጋዜጠኞች መግለጫ እና ማብራሪያ በመስጠት ነው የቀጠለው። እነ እስክንድር ነጋ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሊከሰት ነው እያሉ ለተለያዩ ሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ተቋማት ሲያቀርቡት የነበረው ጥሪ እና ዛሬ ላይ በሀገራችን እየተፈፀመ ያለውን እልቂት፣ በፍትህ ሂደቱ ላይ ያለውን የፖለቲካ ጫናን በተመለከተ እንዲሁም ባልደራስ ይህ ዘመቻው በመንግስት ተፈፃሚ ባይደረግ ምን አይነት ትግል ያካሂዳል?የሚሉ ጥያቄዎች ከጋዜጠኞች ተነስተዋል። መግለጫውን ያነበቡት የባልደራስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር በቃሉ አጥናፉን ጨምሮ የባልደራስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ ለተነሱት ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል። አለም አቀፍ ግብረ ሀይሉም ስለፍትህ የማስፈን ዘመቻው ዛሬ በዙም መግለጫ እንደሚሰጥበት ተገልጧል። ሙሉ መግለጫውን በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply