You are currently viewing ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ነው። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)    ግንቦት 13/2015 ዓ/ም       አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ባልደራስ ለእውነተኛ…

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ነው። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 13/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ባልደራስ ለእውነተኛ…

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ነው። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 13/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በእለተ እሁድ ግንቦት 13/2015 ዓ.ም የአቻ ፓርቲ ተወካዮች፣ ተጋባዥ የክብር እንግዶች እና የተሟላ ነው ተብሎ በምርጫ ቦርድ ተወካዮች የተረጋገጠው የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በተገኙበት በኢትዮጵያ ሆቴል እያካሄደ ይገኛል። የባልደራስ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አምሃ ዳኘው በመድረኩ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የእንኳን ለጠቅላላ ጉባኤው አደረሳችሁ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። በጠቅላላ ጉባኤው ተጋብዘው ከተገኙ አቻ ፓርቲ ተወካዮች መካከል የእናት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳዊት ብርሃኑ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ፕሬዝደንት ፕ/ር ዝናቡ አበራ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ዋና ጸሃፊ ራሄል ባፌ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ ንግግር አድርገዋል፤ አብረን በትብብር እንስራ የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል። ፓርቲው እንዲመሰረት እና ለዚህ ደረጃ እንዲበቃ ያደረገ በሚል ጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ በመድረኩ ከፍ ያለ ምስጋና ቀርቦለታል። ጠቅላላ ጉባኤው አሁንም እየተካሄደ ይገኛል። ቀጥሎም የአመራር አካላት ምርጫ ይካሄዳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply