ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ 125ኛውን የአድዋ ድል በዓልን አስመልክቶ ያዘጋጀው የእራት ግብዣ መርሃ ግብር የድርጅቱ አመራሮች፣ አባላት፣ደጋፊዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙ…

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ 125ኛውን የአድዋ ድል በዓልን አስመልክቶ ያዘጋጀው የእራት ግብዣ መርሃ ግብር የድርጅቱ አመራሮች፣ አባላት፣ደጋፊዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት እየተከናወነ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የ125ኛውን የአድዋ ድል በዓል መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው የእራት ግብዣ መርኃ ግብር በርካታ የሚሆኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ የድርጅቱ አመራሮች፣አባላትና ደጋፊዎች እርስ በርስ በመገባበዝ ረገድ በንቃት የተሳተፉ መሆናቸው ይታወቃል። በዚህም መሰረት ባልደራስ በኤሊያና ሆቴል ባዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ አያሌ የፓርቲው አመራሮች፣አባላት ደጋፊዎችና ተጋባዥ የክብር እንግዶች የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 12 ሰዓት ጀምሮ ተገኝተዋል። ከተጋባዥ እንግዶች መካከል የአብን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጣሂር መሀመድ፣የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊው አቶ ጋሻው መርሻ፣ሳተናው የድሬድዋ ወጣቶች ንቅናቄ ሊቀመንበርና በአሁኑ ሰዓት በድሬድዋ የአብን እጩ ተወዳዳሪ አቶ ሲሳይ አየለ እና ሌሎች የፓርቲው አመራሮች፣ ጋዜጠኛ እና የታሪክ ምሁሩ አቶ ታዲዮስ ታንቱ እንዲሁም ሌሎች ይገኙበታል። በመድረኩ የተገኙት ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱ ስለአድዋ የድል በዓል ንግግር ያደርጋሉ። በዝግጅቱም የሙዚቃ ባንዶች፣የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ጋዜጠኞችና የመድረክ መሪዎችም ተገኝተው መድረኩን እያደመቁ ነው። የእራት ግብዣ መርሐ ግብሩን የማስተዋውቁንና መድረክ መምራቱን ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው የሚያስኬድ ይሆናል። የባልደራስን የፋይናንስ አቅምን ለማጠናከርና የአድዋ ድል በዓልን ለመዘከር ሲባል በዋናነት በፓርቲው የሀብት አፈላላጊ ኮሚቴ በተዘጋጀው የእራት ግብዣ መርሐ ግብር በርካታ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ ከአስተባባሪዎች የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የባልደራስ የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሪት ዘቢባ ኢብራሂም የመክፈቻ ወይም የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን የባልደራስ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊና የምርጫ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ ኢንጅነር ጌታነህ ባልቻ ስለፓርቲው ቁመና አጠር ያለ ንግግር ያደርጋሉ። የእራት ግብዥ ስነ ስርዓቱ ቀጥሎ እንደተጠናቀቀም የባልደራስ ፓርቲ ፕሬዝዳንት የእነ እስክንድር ነጋን ጨምሮ የስንታየሁ ቸኮል፣አስቴር ስዩምና አስካለ ደምሌ ምስል እንዲሁም የእምዬ ምኒልክ እና የእቴጌ ጣይቱ ስዕል ጨረታ ይካሄዳል። የስነ ጹሑፍና የሙዚቃና ስራዎችም በኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና በባህል ቡድን አባላት በየመሃሉ እየቀረቡ ነው። “ሀገር ስታምጥ” የተሰኘው የታጋይ አስቴር ስዩም መፅሀፍም በኤሊያና ሆቴል መግቢያ ላይ ለአንባቢያን እየተሸጠ ነው። የአማራ ሚዲያ ማዕከልም በኤሊያና ሆቴል ተገኝቷል፤ ተጨማሪ መረጃዎችን ወደእናንተ የሚያደርስ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply