ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) “ኢትዮጵያና የዘውግ ፖለቲካዋ” በሚል ርዕስ የውይይት ጉባዔ እንደሚያኪያሂድ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 15 ቀን 2013…

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) “ኢትዮጵያና የዘውግ ፖለቲካዋ” በሚል ርዕስ የውይይት ጉባዔ እንደሚያኪያሂድ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 15 ቀን 2013…

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) “ኢትዮጵያና የዘውግ ፖለቲካዋ” በሚል ርዕስ የውይይት ጉባዔ እንደሚያኪያሂድ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 15 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ “ኢትዮጵያና የዘውግ ፖለቲካዋ” ጉባዔው በሚል ርዕስ ነገ እሁድ ጥር 16 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ 3 ሰዓት ጀምሮ ፒያሳ፤ ቴዎድሮስ አደባባይ ፊት ለፊት በሚገኘው ኤልያና ሆቴል ውስጥ ስብሰባ እንደሚያኪያሂድ ገልጧል። በዚህም የተለያዩ የፖለቲካ ተቋማት ተወካዮችና እውቅ ግለሰቦች እንደሚገኙ ነው ባልደራስ ያስታወቀው። ከ1960ዎቹ ጀምሮ ሰፊ የፓርቲ ፖለቲካ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙትና ‘ሀገራዊ ብሔርተኝነትና ዘውጋዊ ብሔርተኝነት በኢትዮጵያ’ በተሰኘው መፅሐፋቸው የሚታወቁት አቶ አምሀ ዳኘው የመክፈቻ ንግግር ያቀርባሉ ተብሏል። የለውጥ ምጥ በኢትዮጵያ፣ ጋዜጠኝነትና ጋዜጠኛ በተባሉ መፅሐፎቻቸው የሚታወቁትና በተለያዩ ጋዜጦችና መፅሔቶች ለረዥም ጊዜ በጋዜጠኝነት ያገለገሉት አቶ ታዲዮስ ታንቱ እንዲሁም ጥልቅ ፖለቲካዊ ትንታኔዎችን የሚሰጡት ዶ/ር ኤርሴዶ ለደንቦ በጉባዔው ላይ የፖለቲካ ትንታኔ ይሰጣሉ ብሏል ፓርቲው በመልዕክቱ። የባልደራስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ በዕለቱ በሚደረገውን የፓናል ውይይት የምርምር ስራቸውን ያቀርባሉ። በመሆኑም የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙሃን በቦታው ተገኝታችሁ ዝግጅቱን እንድትዘግቡ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply