ባልደራስ ለጠበቆቹ የምስጋና መርሃ ግብር አዘጋጀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ…

ባልደራስ ለጠበቆቹ የምስጋና መርሃ ግብር አዘጋጀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የአደረጃጀት ዘርፍ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ሲሟገቱ ለከረሙት ጠበቆች ለአቶ ሔኖክ አክሊሉ፣ ለአቶ ቤተማርያም አለማየሁ እና ለአቶ ሶሎሞን ገዛኸኝ የምስጋና መርሃ ግብር አዘጋጅቷል። መርሃ ግብሩ ሐሙስ የካቲት 17 ቀን 2014 ዓ.ም በፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ተከናውኗል። ጠበቆቹ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መካከለኛ አመራሮች ፣ አባላትና ደጋፊዎች በሃሰት ሲከሰሱ ከመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች አስከ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ የሕግ ክርክር ሲያደርጉ ቆይተዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ከሰው ተከራክረዋል። ከሦስቱ ጠበቆች መካከል ጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ ደግሞ በጥብቅና ከመከራከርም በዘለለ የኅሊና እስረኞችን በተመለከተ በመገናኛ ብዙሃን የፍርድ ቤቱን ገለልተኛ አለመሆንን የሚያገልጥ ትንታኔ በመስጠታቸው ራሳቸውም በሀሰት ተከሰው ተሟግተዋል ሲል የባልደራስ ሚዲያ ክፍል ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply