ባልደራስ በአዲስ አበባ ጉባዔ እንዳያደርግ መከልከሉን አስታወቀ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-f010-08db23fbbcfc_tv_w800_h450.jpg

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በአዲስ አበባ ጠቅላላ ጉባዔ እንዳላደርግ ተከለከልኩ ሲል ቅሬታ አቅርቧል። ጉባዔው እንዳይደረግ የከለከለው የኦሮሚያ ፖሊስ እንደሆነ ከሆቴሉ እንደተነገረው ፓርቲው አስታውቋል፡፡ ሆቴሉ በበኩሉ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን በኩል ባሰራጨው መረጃ ከባልደራስ ፓርቲ የሥራ ትዕዛዝ እንዳልተቀበለ የገለጸ ሲሆን፣ “ድርጅቱን የከለከለው የፀጥታ አካልም ሆነ የመንግሥት አካል የለም” ሲል አመልክቷል፡፡

የፓርቲውን ክስ በተመለከተ ከአዲስ አበባም ይሁን ከኦሮሚያ ፖሊስ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply