ባልደራስ በእስር ላይ የምትገኘው የፓርቲው አደራጅ የቀለብ/አስቴር ስዩም የጤንነት ጉዳይ እንደሚያሳስበው በመግለፅ ኢሰመኮ እና ኢሰመጉ ተገቢ ህክምና የምታገኝበት ሁኔታ እንዲፈጠር የድርሻቸውን…

ባልደራስ በእስር ላይ የምትገኘው የፓርቲው አደራጅ የቀለብ/አስቴር ስዩም የጤንነት ጉዳይ እንደሚያሳስበው በመግለፅ ኢሰመኮ እና ኢሰመጉ ተገቢ ህክምና የምታገኝበት ሁኔታ እንዲፈጠር የድርሻቸውን እንዲወጡ ሲል አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ዛሬ ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም በእስር ላይ የምትገኘው የፓርቲው አደራጅ የቀለብ/አስቴር ስዩም የጤንነት ጉዳይ እንደሚያሳስበው የሚገልፅ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ (ኢሰመጉ) መጻፉን አስታውቋል። ቀለብ ስዩም በፈጠራ የሽብር ክስ ስለመታሰሯ የገለፀው ባልደራስ ላጋጠማት ከፍተኛ የጀርባ ህመም ተገቢ ህክምና የምታገኝበት ሁኔታ በቃሊቲ ማ/ቤት በኩል አለመመቻቸቱን ገልጧል። በመሆኑም በየትኛውም ሁኔታ ቢሆኑ የዜጎች ህክምና የማግኘት መብታቸው መከበር እንዳለበት የጠቆመው ፓርቲው ኢሰመኮ እና ኢሰመጉ ቀለብ ስዩም እስካሁን ተገቢ ህክምና አለማግኘቷን ተገንዝበው ተፅዕኖ በመፍጠር ረገድ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቋል። የቀለብ ስዩም ባለችበት የቃሊቲ ማ/ቤት ላጋጠማት የጀርባ ህመም ተገቢ ህክምና እንድታገኝ ከመተባበር ይልቅ ረዥም ቀጠሮ በመቅጠር ህመሟ እንዲባባስባት እያደረገ ነው ሲሉ ቤተሰቦቿ ከአሁን ቀደም መግለጻቸው ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply