ባልደራስ በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ እና ወራሪ ጠላትን ፊት ለፊት እየተፋለሙ ላሉ የወገን ጦር አባላት በዓይነት እና በገንዘብ ሲያሰባስብው የነበረውን ድጋፍ ለማድረስ በሦስት አቅጣጫ ጉዞ…

ባልደራስ በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ እና ወራሪ ጠላትን ፊት ለፊት እየተፋለሙ ላሉ የወገን ጦር አባላት በዓይነት እና በገንዘብ ሲያሰባስብው የነበረውን ድጋፍ ለማድረስ በሦስት አቅጣጫ ጉዞ መጀመሩን አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን እና ከአሸባሪው የወያኔ ኃይል ጋር ፊት ለፊት እየተፋለሙ ላሉት የወገን ጦር አባላት ያሰባሰበውን ድጋፍ በ3 አቅጣጫዎች ማሰራጨት መጀመሩን አስታውቋል። “እንደ አቅሜ፤ ድጋፍ ለሀገሬ !” እኔ እያለሁ ወገኔ አይደፈርም፤ አይራብም፤ አይሰደድም ! በሚል መርህ ቃል በገንዘብ እና በዓይነት ያሰባሰባው ግምቱ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሆነ የዓይነት ድጋፍን ለማድረስ ነው እየተጓዘ ያለው። የድጋፍ ስርጭቱም:_ 1) ከአዲስ አበባ – አፋር፣ 2) ከአዲስ አበባ – ደብረ ብርሃን – ሸዋ ሮቢት _ደሴ 3) ከአዲስ አበባ – ደብረ ማርቆስ – ጎንደር መሆኑን አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply