You are currently viewing ባልደራስ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን በአቶ ስንታየሁ ቸኮል ጉዳይ ላይ መግለጫ እንዲሰጥ ጠየቀ! ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የባልደራስ ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመ…

ባልደራስ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን በአቶ ስንታየሁ ቸኮል ጉዳይ ላይ መግለጫ እንዲሰጥ ጠየቀ! ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የባልደራስ ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመ…

ባልደራስ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን በአቶ ስንታየሁ ቸኮል ጉዳይ ላይ መግለጫ እንዲሰጥ ጠየቀ! ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር የባልደራስ ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት ጥቅምት 2/2015 ዓ.ም. በአቶ ስንታየሁ ቸኮል የእስር ሁኔታ ላይ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሥራ ሓላፊዎቸ ጋር በኮሚሽኑ ጽ/ቤት ሰፊ ውይይት አካሂደዋል። የባልደራስ ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ አባልና የድርጅት ጉዳይ ሓላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ላለፉት 5 ወራት በአማራ ክልል፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ወህኒ ቤቶች በግፍ እየተሰቃዩ መሆናቸውን የባልደራስ ተወካዮች ለኮሚሽኑ ባለሥልጣናት አብራርተዋል። ፍርድ ቤቶች ከአንዴም አምስት ስድስት ጊዜ በነፃ የለቀቋቸውን የግፍ እስረኛውን አቶ ስንታየሁ ቸኮልን፣ ፖሊሶች ከፍትህ ሥርዓቱ አሠራር ውጭ ከፍርድ ቤት ደጃፍ ላይ እያፈኑ ከአንድ እስር ቤት ወደሌላ እስር ቤት እያንከራተቷቸው መሆኑ በባልደራስ ሰዎች ተገልጿል። ፖሊሶች በተለያዩ ጊዜያት የገዢውን ፓርቲ ፖለቲካዊ ፍላጎት የሚያሳካ ክስ እየመሠረቱ ሰብኣዊ መብቶቻቸውን መግፈፋቸውና ቤተሰቦቻቸውንም ማጉላላታቸው እጅግ አሳዛኝ መሆኑ በውይይቱ አንስተዋል። የባልደራስ አመራሮች፣ ፖሊስ የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ፍላጎትና ውሳኔዎች አስፈፃሚ መሣሪያ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ ተገንዝቦ በአቶ ስንታየሁ ቸኮል ላይ የሚያደርሰውን ለከት ያጣ እስርና የህግ ጥሰት አስመልክቶ በአፋጣኝ መግለጫ እንዲሰጥ አቤቱታቸውን አቅርበዋል። በተጨማሪም የባልደራስ አመራሮች ኮሚሽኑ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በእስር ላይ እያሉ የሚደርስባቸውን ማንኛውንም ዓይነት የሰብኣዊ መብት ጥሰት ለመከላከል እያደረገ ያለውን ክትትል አመስግነዋል። መጨረሻም የኮሚሽኑ ሓላፊዎችና ባለሞያዎች በበኩላቸው፣ የአቶ ስንታየሁ ቸኮል ኢሰብአዊ የሆነ የእስር ሁኔታ ኮሚሽኑም ለመከታተል እስኪያስቸግረው ድረስ ግራ ያጋባው መሆኑን አብራርተዋል። አያይዘውም ጉዳዩን በቅርብ በመከታተል ተጨማሪ መረጃዎችን በመሰብሰብና በማጠናቀር የኮሚሽኑ ዋና ሓለፊዎች መግለጫ እንደሚሰጡበት ቃል ገብተዋል ሲል ባልደራስ አስታውቋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply